126ኛው የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)126ኛው የአድዋ ድል በዓል “አድዋ ለኢትዮጵያዊያን ህብረት የአፍሪካ የነጻነት ጮራ!” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ በአድዋ ጦርነት የውጭ ወራሪ የነበረው የጣሊያን ጦር ድባቅ ተመቶና ሽንፈትን ተከናንቦ የተመለሰበት መሆኑን አውስተው፥ ድሉ ለአፍሪካዊያንም ትልቅ ድል መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
በዓሉ ከየካቲት 15 – 23/ 2014 ዓ.ም በኪነ ጥበብ ዝግጅቶች፣ ፓናል ውይይት ፣በሁሉም የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ሚሲዮኖች የተለያዩ ዝግጅቶች አውደ ርዕይ እና ዓውደ ጥናት የሚከበር ሲሆን ፥ በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮችም በተለያየ ደረጃ የሚከበር መሆኑንም አብራርተዋል።
ሁሉንም ተግባራት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በድምቀት እንደሚከበር መገለፁንም ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!