Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች መልሶ ግንባታ ላይ የሚያተኩሩ የ11 ፕሮጀክቶች የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች መልሶ ግንባታ ላይ የሚያተኩሩ 11 ፕሮጀክቶች የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።
ፕሮጀክቶቹ ከወቅቱ የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታና ጦርነቱ ካስከተለው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊና አካባቢያዊ ጉዳቶች በመነሳት የተቀረጹ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም በዩኒቨርሲቲው ያሉ ሁሉም ኮሌጆችና ኢንስቲቲዩቶች እያንዳንዳቸው አንድ የፕሮጀክት ጽንሰ-ሃሳብ በመቅረጽ በኮሌጅ አካዳሚክ ስታፍ፣ በኮሌጅ የምርምርና ስነ-ምግባር ኮሚቴ፣ በዲኖች ካውንስልና በማዕከል ተመርጠው ለትግበራ መዘጋጀታቸውን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ቢኒያም ጫቅሉ ተናግረዋል፡፡
ከተቀረጹት ፕሮጀክቶች መካከል የተቀናጀ የመልሶ ማገገም አገልግሎት መስጠትና እና የጤና ጥበቃ ስርዓቶችን ማሻሻል፣ ጦርነቱ በጎዳቸው ቦታዎች የሚገኙ የቢዝነስ ኢንተርፕርይዞችን ቶሎ እንዲያግሙ ማገዝ፣ የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ባህልና ማንነትን ማጥናት፣ ማስተዋወቅና ወደነበረበት መመለስ፣ ለተጎዱ አካባቢዎች እንሰሳትን መሰረት ያደረገ የማገገሚያ ድጋፍ መስጠት፣ በጦርነት ለተጎዱ የህክምና እቃዎች፣ የውሃ አቅርቦት፣ የመካኒካል ቁሳቁሶች ጥገና እና ተከላ መስራት ይገኙበታል።
በተጨማሪም በጦርነት የተጎዱ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን መደገፍ፣ የሳይንስ ቤተ-ሙከራዎችን ተግባራዊ ማድረግ፣ ለተጎዱ አካባቢዎች ተስፋ ሰጭ የግብርና ቴክኖሎጅዎችን እና ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት እንዲያገግሙ ማድረግ፣ የተሻሻሉ የሰብል ቴክኖሎጂዎችን በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች በማስገባት ግብርናን ማገገም፣ ጦርነቱ በጎዳቸው አካባቢዎች ኮምፒዩተሮችን መጠገንና መረጃዎችን እንደገና መሰብሰብ/ማከማቸት፣ ለተጎዱ አካባቢዎች ትምህርትን እንደገና ማደራጅት ናቸው፡፡
የማህበረሰብ መልሶ ማቋቋምና መደገፍ ፕሮጀክቶች ላይም ግምገማና ውይይት ተደርጎ ወደ ትግባር ለመግባት በቂ ቁመና ላይ መሆናቸው መገለጹን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.