Fana: At a Speed of Life!

አቶ ብናልፍ አንዱዓለም በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ከሆኑት ኢቶ ታካኮ ጋር በሁለትዮሽ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መገንባት፣ ብሄራዊ መግባባት መፍጠር እና የተፈናቀሉ ዜጎችን ሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋምን አስመልክቶ እስከ አሁን በተሰሩ እና ቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ ማብራሪያ መስጠታቸው ተገልጿል፡፡
አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በበኩላቸው፥ ሀገራቸው ጃፓን በቀውስ ጊዜ ስራ አስተዳደር ሰፊ ልምድ ያላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው የጃፓን ዩኒቨርሲቲዎችን ከኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በማስተሳሰር በሰላም አስተምህሮ ላይ በጋራ መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡
በሀገራዊ ምክክሩና በሰብዓዊ ድጋፍ እንዲሁም በመልሶ ማቋቋም ሂደት አስፈላጊ በሆኑ መስኮች ድጋፍ ለማድረግ የጃፓን መንግስት ዝግጁ መሆኑን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.