Fana: At a Speed of Life!

አቶ መላኩ አለበል የኮሪያ እውቅ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የኮሪያ እውቅ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የኮሪያ አምባሳደር ካንግ ሲዮክሂን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያና ኮሪያ የጠበቀና የቆየ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትስስር ያላቸው ሀገራት ናቸው ፡፡
የኮሪያ መንግስት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት የሚያደርገውን ድጋፍ ያደነቁት አቶ መላኩ ፥ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በኮሮና ወረርሽኝ የደረሰበትን የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ወደ ነበረበት ለመመለስ ያደረገው ድጋፍ ለስራ ዕድል ፈጠራና የዘርፉን ውጤታማነት በተሻለ መንገድ ለማስቀጠል ሚናው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያና ኮሪያ ከንግድ ግንኙነት በላይ የላቀ ወንድማማች ህዝቦች ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ከ100 ሚሊየን በላይ ህዝብ ያላት፣ ያልተነካ የተፈጥሮ ህብት ባለቤት፣ ምቹ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ባለቤት በሆነች ሀገር ላይ መዋለ ንዋይን በማፍሰስ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ መስራት የአፍሪካን ገበያ መቆጣጠር መሆኑን በመገንዘብ የኮሪያ እውቅ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም ፥ ኮሪያዊያን በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ያላቸውን መልካም ተሞክሮ በመጋራት የተሻለና ውጤታማ ስራ ለመስራት በአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ በቆዳና ጨርቃጨርቅ ዘርፉ የአቅም ግንባታ ስራ እንዲደግፉ፤ የኮሪያ ኢግዚት ባንክ ለተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገባውን ገንዘብ በመስጠት ወደስራ እንዲገባ ፤ ከኮይካ ጋር የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ የእሴት ሰንሰለት ልማት ለመደገፍ የተገባው ስምምነትም ወደ ተግባር እንዲቀየር እንዲያደርጉ አምባሳደሩን ጠይቀዋል፡፡
መንግስት በአምራች ዘርፉ ለመሰማራት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ኮሪያዊያን ኩባንያዎችና ባለሃብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቅሰው ፥ የጉምሩክና ታክስ ሂደቱን ቀለል ባለ መልኩ የሚያስፈፀም ቡድን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተቋቁሞ ወደስራ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የኮሪያ አምባሳደር ካንግ ሲዮክሂ በበኩላቸው ፥ ኢትዮጵያ ከሀገራቸው ኮሪያ ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኮሪያዊያን አምራቾች እየተደረገላቸው ያለውን ድጋፍ በማድነቅ አሁንም እያጋጠማቸው ያለውን ችግሮች በጋራ በመሆን እንዲፈታ የጠየቁት አምባሳደሩ ፥ ሌሎች ትላልቅ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በኢንቨስትመንት ዘርፉ እንዲሰሩ ለማድረግ ኢትዮጵያ ለአምራች ኢንዱስትሪ ያላትን አመችነት ኢንደሚያስረዱ ቃልመግባታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.