“ማጀቴ” የተሰኘው አዲስ የሙዚቃ አልበም በመጪው ሐሙስ ለአድማጭ ይደርሳል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በሻኩራ ሪከርድስ የተዘጋጀው “ማጀቴ” የተሰኘው አልበም በመጪው ሀሙስ ለአድማጭ እንደሚደርስ አዘጋቾቹ ዛሬ በቀነኒሳ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
ይህ አልበም የራፕ ዘፈኖችን በማቀንቀን የምትታወቀው ኒና ግርማ የመጀመሪያ አልበም ሲሆን፥ በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስራዎችንም አካቷል።
በካሙዙ ካሳ የተቀናበረው የማጀቴ አልበም የግጥም እና ዜማ ድርሰት በኒና ግርማ የተሰራ እንደሆነና በሻኩራ ሪከርድስ አማካይነት ፕሮዲዩስ እንደተደረገም ተገልጿል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!