Fana: At a Speed of Life!

አፍሪ-ኤግዚም ባንክ የአፍሪካን የንግድ ትስስር ለማሳደግ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ በእጥፍ ሊያሳድግ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪ-ኤግዚም ባንክ የአፍሪካን የንግድ ትስስር ለማሳደግ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ በእጥፍ የሚያሳድግ መሆኑን የባንኩ ፕሬዚዳንት ገለጹ።
የአፍሪ-ኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ቤኔዲክት ኦርማህ በተለይ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ባንኩ የገንዘብ አቅሙን በማሳደግ የአህጉሪቷን የንግድ ትስስር ለማጎልበት በልዩ ትኩረት ይሰራል።
የአፍሪካ ህብረት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ባንኩ ዓመታዊ የገንዘብ ምጣኔውን ወደ 6 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር እንዲያድግ መደረጉን ገልጸዋል።
የአህጉሪቷን የንግድ እንቅስቃሴ ለመደገፍ በሚያስችል መልኩ ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ ለተለያዩ አገራት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
የአፍሪካን ወጪና ገቢ ንግድ ለመደገፍ የተቋቋመ ባንክ በመሆኑ የአገሮችን የንግድ እንቅስቃሴ በገንዘብ የመደገፍና የማበረታታት ኃላፊነት አለበት ብለዋል።
የአህጉሪቱን እድገት ለማሳለጥ የንግድና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ የብድር፣የመድህንና ሌሎች የፋይናንስ ድጋፎችን ያደርጋል ነው ያሉት።
የኢንፖርት ኤክስፖርት ባንክ የሆነው አፍሪ-ኤግዚም ባንክ ለአፍሪካዊያን ተጠቃሚነት በአፍሪካ መንግስታት የተቋቋመ በመሆኑ ሌሎች መደበኛ ባንኮች ማከናወን የማይችሉትን ክፍተት እየሞላ መሆኑን ፕሮፌሰር ቤኔዲክት አብራርተዋል።
አፍሪ-ኤግዚም ባንክ ባለፉት አምስት ዓመታት የአፍሪካን የንግድ እንቅስቃሴ ለመደገፍ 20 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ፈሰስ ማድረጉን አስታውሰዋል።
በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ደግሞ በእጥፍ የማሳደግ እቅድ መያዙን ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።
የኢንፖርት ኤክስፖርት ባንክ የሆነው አፍሪ-ኤግዚም ባንክ እ.ኤ.አ. በ1993 በአፍሪካ ልማት ባንክ ስር የተፈጠረ የፓን አፍሪካ ባለብዙ ወገን የንግድ ፋይናንስ ተቋም ነው።
አፍሪ-ኤግዚም ባንክ በኢትዮጵያ ንግድና ኢንቨስትመንት፣የስራ እድል ፈጠራ እና ድህነት ቅነሳ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እየደገፈ ይገኛል።
በቅርቡም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር 1 ቢሊየን ዶላር ብድር ማግኘት የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.