Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራው ሀገራዊ ጥሪውን ተከትሎ ባደረጋቸው ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎዎች 22 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ ተገኝቷል – ዳያስፖራ ኤጀንሲ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው ሀገራዊ ጥሪውን ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት በመምጣት ባደረጋቸው ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎዎች 22 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን የዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ እንድሪስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ በተለይም የዳያስፖራው ወደ ሀገር ቤት መምጣት በፐብሊክ ዲፕሎማሲው ዘርፍ ስኬት የተገኘበት ነበር ብለዋል።
ዳያስፖራው ወደ ሃገር ቤት መምጣቱ የእርስ በእርስ ትውውቅ እንዲኖረው እና የሃገር አምባሳደርነቱ አጠናክሮ እንዲቀጥል ያገዘ መሆኑንም ዶክተር መሀመድ አንስተዋል።
ከገጽታ ግንባታ ባለፈም እስካሁን ከቀጥተኛ ተቋማት በተሰበሰበ መረጃ ብቻ ከአየር ትኬት፣ ከአገልግሎት ዘርፎች እና ከቪዛ አገልግሎት 33 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር መገኘቱን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ለሰብዓዊ ድጋፍ 239 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በድጋፍ መልክ አበርክተዋል።
ዳያስፖራው በሀገሩ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ ከዘርፍ ተኮር ማብራሪያ ጋር እንዲያገኝ እንዳስቻለውም ተጠቅሷል።
እስካሁን በተጠናቀረ መረጃ መሰረት 450 የዳያስፖራ አባላት የኢንቨስትመንት ጥያቄ አቅርበው ወደ እንቅስቃሴ ገብተዋል።
ከዚሁ ጋር በተገናኛ የቢሮክራሲ ችግሮችን ለመፍታት ተቋማት የጋራ ጥረት እያደረጉ ነውም ተብሏል።
ዳያስፖራው በማዕከልና በክልሎች በተዘጋጁ 55 ሁነቶች ላይ መሳተፉ የተገለጸ ሲሆን÷ ከ”በቃ” የጎዳና ላይ ሰልፍ ውጪ ሌሎቹ መከናወናቸው ዶክተር መሀመድ ተናግረዋል።
ጥሪው ዓመቱን ሙሉ የሚዘልቅ በመሆኑ ተጨማሪ ስኬቶች እንደሚመዘገቡም ይጠበቃል ነው ያሉት።
በምስክር ስናፍቅ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.