የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል የዛሬው ሰኞ የሀገሪቱ የድል በዓል አንዲሆን ወሰኑ
አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል የሀገሪቱ ብሄራዊ ቡድን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ ድሉን ለማክበር የዛሬው ሰኞ ብሄራዊ በዓል አንዲሆን ወስነዋል።
ሀገራቸው ሴኔጋል ግብፅን በመለያ ምት 4 ለ 2 በማሸነፍ ዋንጫውን ስታነሳ በ 35ኛዉ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የነበሩት ማኪ ሳል የዛሬውን ሰኞ የሀገሪቱ የድል በዓል አንዲሆን መወሰናቸውን በሀገሪቱ ቴሌቪዥን አስታውቀዋል፡፡
አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ማኪ ሳል በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ኮሞሮስን ሊጎበኙ የነበረ ቢሆንም ድል ያደረጉትን የትሪንጋ አንበሶች ለመቀበል ወደ ሴኔጋል ዳካር መብረራቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡
የትሪንጋ አንበሶቹ በነገው እለት በሴኔጋል ዳካር በሚገኘው ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግስት ዳጎስ ያለ ሽልማት ይጠብቃቸዋልም ተብሏል፡፡
በመሆኑም በዛሬው እለት የሀገሪቱ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ዝግ ሲሆኑ÷ ሴኔጋላውያን በሀገሪቱ የእግር ኳስ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የአፍሪካ ዋንጫ ድል በማክበር ላይ ይገኛሉ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!