የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን ደቡብ አፍሪካዊው ቪክቶር ጎሜዝ በዋና ዳኝነት ይመሩታል
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካዊው ኢንተርናሽናል አልቢትር ቪክቶር ጎሜዝ ዛሬ ሴኔጋልና ግብፅ የሚያደርጉትን የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ እንዲዳኙ በካፍ መመረጣቸው ተገልጿል።
ደቡብ አፍሪካዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ቪክቶር ጎሜዝ ከፈረንጆቹ 2008 ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ ሊግ የሚደረጉ ታላላቅ ጨዋታዎችን መርተዋል፡፡
ቪክቶር ጎሜዝ ከ 2013-2019 የተካሄዱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን በዋና ዳኝነትመምራታቸውም የሚታወስ ነው፡፡