Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለሶርያ አሸባሪ ድርጅት የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ጦር አዛዥ የነበሩት ቤን ሆጅስ ዩናይትድ ስቴትስ ዋይፒጅ /ፒኬኬ ለተባለው የሶርያ አሸባሪ ድርጅት የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም ጠይቋል ፡፡

የቀድሞ የአሜሪካ ጦር አዛዥ ቤን ሆጅስ ፥ አሜሪካ በሶሪያ ለሚገኙ አሸባሪ ድርጅቶች የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም ጠይቀዋል፡፡

የቀድሞው የጦር አዛዥ ከሁድሰን ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ባልደረባ ከሆኑት ሚካኤል ዶራን ጋር በበይነመረብ ውይይት ባደረጉበት ጊዜ እንደተናገሩት ፥ አሜሪካ ለሶሪያው አሸባሪ ቡድን ዋይፒጅ የምታደርገው ድጋፍ ቱርክን አስቆጥቷል ፡፡

ሆጅስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ ወደ ቱርክ አቅንተው ፥ ከቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጋር በጉዳዩ ዙርያ እንዲወያዩ መክረዋል፡፡

በአሸባሪ ቡድኑ ምክንያት የቱርክ ደህንነት አደጋ ላይ ቢወድቅም አሜሪካ ግን ግድ ሳይሰጣት አሁንም ቡድኑን መደገፍ እንዳላቆመች ዘገባው አስታውሷል፡፡

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ፥ ‘‘አሜሪካ የዳኢሽ አሸባሪ ድርጅትን ለመዋጋት በሚል ዓላማ ለዋይፒጅ የምትሰጠውን ድጋፍ አንዱን አሸባሪ ቡድን ለመዋጋት ሌላውን መደገፍ ትርጉም አይሰጥም’’ ሲሉ የአሜሪካን አግባብ ያልሆነ አካሄድ ነቅፈውታል ሲል ቲአርቲ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.