Fana: At a Speed of Life!

ሥራ ፈጣሪና ሀብት አመንጭ ለሆኑ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል- ዶክተር በለጠ ሞላ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቴክኖሎጂ ዘርፍ ሥራ ፈጣሪና ሀብት አመንጭ ለሆኑ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ፈጣራዎች እና እምቅ አቅምና ክህሎት ላላችው ድጋፍና ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ ገለጸ፡፡

የአገር አቀፍ የፈጠራ ባለሙያዎችና የስታርታፖች መድረክ የተካሄደ ሲሆን÷የኢኖቬሽን ምርምር ድጋፍ ማመልከቻና ማሳወቂያ ፓርታል ተመርቋል፡፡

በመድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ የተገኙ ሲሆን÷ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በሀብት ማመንጨትና በስራ ፈጠራ ዘርፍ ብዙ ስራ የሚጠብቃቸው ሀገራት የነገ እድገታቸው የተሳካ ይሆን ዘንድ ዛሬ ላይ ለጀማሪ ቢዝነሶችና ለቴክኖሎጂ ስራ ፈጣሪዎች በሚሠጡት ድጋፍ፣ ማበረታቻና ጥበቃ የተመሠረተ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በመላ ሀገሪቱ ቴክኖሎጂና ፈጠራን ማዕከል ያደረጉ ስራዎች ላይ በስፋትና በቀጣይነት በትኩረት ይሰራልም ብለዋል፡፡

የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አንዱና ዋና ተግባሩ የፈጠራ ሀሳብን እና ኢኖቬሽንን ማበረታታት፣ መደገፍ እና ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነው ያሉት ደግሞ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ ናቸው፡፡

ለዚህ ተግባር መሳካት ስታርታፖዎች፤ ኢኖቬተሮች እና ኢንተርፕረነሮች ዋና ተዋናይ ናቸው ያሉት ሚኒስቴር ዲኤታው÷የኢንኩቤሽን ማዕከላት፣ አክሲለረተሮች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍና የመንግስት ተቋማት ተቀናጅተው አጠቃላይ የኢኖቬሽን ስርዓተ-ምህዳር እንዲፈጠር ገንቢ ሚና መጫዎት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

አሰራርን የሚያሻሽሉ ምቹ ፖሊስዎችን እና ሌሎች ተያያዥ ሁኔታዎችን በመፍጠር የተቀናጀና መጠነ ሰፊ ተግባራት ማከናወን እንዳለባቸው መገለጹን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.