Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪ ህውሓት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ መገንባትና የተፈናቀሉ ዜጎችን ማቋቋም ለክልሎቹ የሚተው አይደለም – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪ ህውሓት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ መገንባትና የተፈናቀሉ ዜጎችን ማቋቋም ለክልሎቹ የሚተው አይደለም ሲሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ በአሸባሪ ህውሓት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ከመገንባትና የተፈናቀሉ ዜጎችን ከማቋቋም አንፃር ሁሉም የበኩሉን ድረሻ መወጣት እንደሚገባ አመላክተዋል።

በሀረሪ ክልል ሀገራዊ ህልውና ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የልማት ስራዎችን በትኩረት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጸው ፥ በተለይም የቱሪዝም ዘርፉን በማስተዋወቅና በዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማጎልበትና የስራ እድል ለመፍጠር የላቀ ትኩረት እንደተሰጠው ነው የጠቆሙት።

በዘንድሮው ዓመት በግብርናው ዘርፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ፥ በተለይም የስንዴ ሰብልን ለማሳደግ ካለፉት ዓመታት በተለየ መልኩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

በቀጣይም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

በብሔርና በሃይማኖት ሽፉን በህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ፍላጎት እንዳይሳካ ማክሸፍ ያስፈልጋልም ነው ያሉት አቶ ኦርዲን።

ከዚህ ባሻገር በአሸባሪ ህውሓት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ መገንባትና የተፈናቀሉ ዜጎችን ማቋቋም ለክልሎቹ የሚተው እንዳልሆነ አንስተው ፥ ሁሉም የበኩሉን ሃላፊነት መወጣትና እገዛ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በተለይም በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እንዳይከሰት የሁሉም ርብርብ አስፈላጊ መሆኑን መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.