Fana: At a Speed of Life!

የጤናውን ዘርፍ ለማገዝ የተሰራው የትራፊክ ማኔጅመንት ሞባይል መተግበሪያ የ “ሁዋዌ ቴክ ፎር ጉድ” ውድድር አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ጥር 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦንላይን በተካሄደው ምርጫ አብላጫ ድምፅ በማግኘት የመጀመሪያውን የሁዋዌ “Tech4Good” ውድድር “Are U OK?” በሚል መጠሪያ የተወዳደረው የታይላንድ ቡድን ማሸነፉን ኩባንያው አስታውቋል፡፡

አሸናፊው የታይላንድ ቡድን የአንደኛነት ደረጃን እንዲጎናፀፍ የረዳው  “Turning green” የሚል ስያሜ የሰጠው የሞባል መተግበሪያ ፕሮጀክት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የሞባይል መተግበሪያውም የሆስፒታሎችን እና የመንግስት የጤና ተቋማትን ሥራዎች ለማቅለል የተሰራ እንደሆነም ነው ከኩባንው ያገኘነው መረጃ ያመላከተው፡፡

መተግበሪያው ለአምቡላንሶች ያልተጨናነቁ መንገዶችን በመጠቆም የትራፊክ ማኔጅመንቱን ለማገዝና በትራፊክ አደጋና መጨናነቅ ምክንያት የሚደርስ ሞትን ለመቀነስ ታልሞ የተሰራ መሆኑም ተነግሯል፡፡

አሸናፊዎቹ 20 ሺህ  የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ሽልማት ይበረከትላቸዋል ነው የተባለው፡፡

በተጨማሪም ከሁዋዌ ከፍተኛ አመራር ጋር የ60 ደቂቃ ወርክሾፕ እና ግኝታቸውን ለባለሀብቶች የማቅረብ እውን ማድረግ የሚችሉበት አጋጣሚም ይፈጠርላቸዋል፡፡ አሸናፊዎቹ ትላልቅ መድረኮች ላይ ንግግር የማድረግ እድልም ያገኛሉ ያለው የሁዋዌ ኩባንያ ነው፡፡

በሁለተኛነት እና በሦስተኛነት ያጠናቀቁት ተወዳዳሪዎችም በቅደም ተከተል  የ15 ሺህ እና የ10 ሺህ ዶላር ተሸላሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በፈረንጆቹ በ2008 የተመሰረተው የሁዋዌ “Seeds for the Future”  ፕሮግራም በአገራትና በባህል መካከል ያለውን የክህሎት፣ አገር ውስጥ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና የተግባቦት ክፍተቶችን ለማጥበብ ያለመ ነው፡፡

የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን እና ቴክኖሎጂ እውቀት እና ልምድን ለዓለም አቀፍ ቢዝነስ በማጋራት በተለያዩ ሀገራት ያሉ ታዳጊዎች በኢንዱስትሪው ስላሉ የላቁ ቴክኖሎጂዎች መማር እንዲችሉ እድል ይፈጥራል፡፡

ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ ሁዋዌ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 10 ተማሪዎችን በመምረጥ ለሁለት ሳምንታት የህዋዌ ዋና መስሪያ ቤት ወደሚገኝበት ቻይና እየላከ ስልጠና ላይ እንዲሳተፉና የባህልና ቴክኖሎጂ የልምድ ልውውጥ እንዲደርጉ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ይሁን እንጂ የኮቪድ- 19 ወረርሽኝን ተከትሎ ከእ.ኤ.አ 2020 አንስቶ ፕሮግራሙን በኦንላይን ብቻ መሰጠት የተጀመረ ሲሆን፥ የ2021 መርሀ ግብሩም በኦንላይን ተካሂዶ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተሳተፉ 40 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ትምህርቶቹ መሰረታዊ እና የላቀ ደረጃ ያላቸው እንደ 5ጂ ፣ ክላውድ ኮምፒቲንግ  እና  አርቴፊሻል ኢንተለጀንሲ ያሉ ዋና ዋና ቴክኖሎጂዎች ላይ የሚያተኩሩ እንደሆኑ ተመላክቷል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.