Fana: At a Speed of Life!

ጠበቆች ሙያዊ ሚናቸውን በሚገባ እንዲወጡ የጠበቆች ማህበር መቋቋሙ እጅግ ጠቃሚ ነው – ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠበቆች ሙያዊ ሚናቸውን በሚገባ እንዲወጡ የጠበቆች ማህበር መቋቋሙ እጅግ ጠቃሚ ነው ሲሉ የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር በታሪኩ የመጀመሪያውን የማህበሩን ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዷል፡፡
ጉባኤው ወይዘሮ ስንዱ ዓለሙን የማህበሩ ኘሬዚደንት እንዲሁም አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸውን ምክትል ኘሬዚደንት በማድረግ መርጧል።
በተመሳሳይ ወ/ሮ ሂሩት መለሠ፣ አቶ ፊሊጶስ አይናለም፣ አቶ ሊቁ ወርቁ፣ አቶ ዮሴፍ አዕምሮ፣ ወ/ሮ ሆሳና ነጋሽ፣ ወ/ሮ ትደነቂያለሽ ተስፋ እና አቶ ሰለሞን እምሩ የስራ አስፈጻሚ አባል በመሆን ተመርጠዋል፡፡
ሚኒስትሩ ጉባኤው ታሪካዊ መሆኑን አውስተው ፥ ጠበቆች ሙያዊ ሚናቸውን በሚገባ እንዲወጡ የጠበቆች ሙያዊ ብቃት እና ሥነ-ምግባር ከፍ ያለ እንዲሆን ባለሙያዎችን የሚደግፍ እና እርስበርስ በመተራረም እና በመማማር እንዲያድጉ ሁሉም ባለሙያ አባል የሆነበት፣ የቁጥጥር፣ የክትትል ሥልጣን እና ኃላፊነት ያለው በሕግ የተቋቋመ የጠበቆች ማህበር መቋቋሙ እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ማህበሩ ኃላፊነቱን በብቃት በመወጣት የጥብቅና ሙያ የተከበረ እንዲሆን፣ በብቃታቸው እና በሥነ-ምግባራቸው ስመጥር የሆኑ ጠበቆች እንዲበዙ እና ጎልተው እንዲወጡ ከማህበሩ ጋር በቅርበት ለመሥራት ያላቸውን ፈቃደኝነት እና ዝግጁነት ገልጸዋል ሚኒስትሩ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.