የጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) በታህሳስ ወር የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወርም ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ÷ በጥር ወር 2014 ዓ.ም የአውርፕላን ነዳጅን ጨምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም ሲሸጥበት በነበረው ያለምንም ለውጥ በነበረበት እንዲቀጥል መወሰኑን ገልጿል፡፡
በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችል መሆኑንም አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!