Fana: At a Speed of Life!

በኒጀር እርዳታ ለመቀበል ሲጠባበቁ የነበሩ 20 ሰዎች በመረጋገጥ አደጋ ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኒጀር እርዳታ ለመቀበል ሲጠባበቁ የነበሩ 20 ሰዎች በመረጋገጥ አደጋ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በኒጀር ዲፋ በተሰኘች ከተማ እርዳታ ለመቀበል ሲጠባበቁ በነበሩ ሰዎች በተፈጠረው መረጋገጥ 20 ሰዎች ለህልፈት የተዳረጉ ሲሆን ÷ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ ሴቶች እና ህፃናት ናቸው ተብሏል፡፡

እንዲሁም ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም ሌሎች አስር ሰዎች ቆስለዋል፡፡

ይህ የመረጋገጥ አደጋ የተፈጠረው የእርዳታ መስጫ ድርጅቱ  በር ሲከፈት ቀድሞ ለመግባት በተደረገ ሙከራ ነው፡፡

በአካባቢው በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ቦኮሃራም በፈፀመው ተዳጋጋሚ ጥቃት የተፈናቀሉ 120 ሺህ ያህል ሰዎች ይገኛሉ ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.