ከአመት በፊት ውሃ መጠጣት ያቆመችው ሴት ካጋጠማት የጤና ችግር እያገገመች ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአንድ ዓመት በፊት ውሃ መጠጣት ያቆመችው ታማሚ ጤንነቷ መሻሻል ማሳየቱ ብዙዎችን አስገርሟል።
የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት በቀን እስከ ሁለት ሊትር ውሃ መጠጣት በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች አሉት።
ሶፊያ ፓርቲክ የተባለችው የ35 ዓመት ሴት ግን የታሸገም ሆነ የፈላ ውሃ መጠጣት ካቆመች አንድ ዓመት አልፏታል።
ሶፊያ ፓርቲክ ከአንድ ዓመት በፊት በመገጣጠሚያ ጡንቻዎች ህመም፣ በምግብ አላርጂ፣ በምግብ አለመፈጨት ችግር እና በቆዳ በሽታ ህመም ትሰቃይ ነበር።
ከምትሰቃይበት ህመም ለመፈወስም በተደጋጋሚ ወደ ሆስፒታል በማቅናት ያደረገችው ህክምና ለውጥ ሊያመጣላት አልቻለም።
ይህን ተከትሎም የስርዓተ ምግብ ባለሙያ በማማከር፥ ከዚህ በፊት ትከተለው የነበረውን የአመጋገብ ስርዓት ለመቀየር ትወስናለች።
ከዚህ ጋር ተያይዞም በባለሙያ ምክር ደረቅ ምግቦችን ታዘወትራለች፤ ከአዲሱ አመጋገቧ ጋር ተያይዞም ውሃ ከመውሰድ ትቆጠባለች።
በዚህ ሂደት ውስጥም ጤናዋ መሻሻል ያሳየ ሲሆን፥ ከቀናት ቆይታ በኋላ ከነበሩባት የጤና እክሎች እያገገመች መምጣቷን ትናገራለች።
ውሃ መጠጣት ካቆመችበት ጊዜ ጤናማ ህይዎት አለኝ የምተለዋ ሶፊያ ጉዳዩ እንግዳ መሆኑንም ትጠቅሳለች።
በጉዳዩ ላይም ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልገው ገልጻለች።
ምንጭ፦ ኦዲቲ ሴንትራል
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision