Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ኮቪድ-19 የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ8 ነጥብ 8 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ታኅሣሥ 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እጅግ እየተስፋፋ እንደሆነና በሽታው የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ8 ነጥብ 8 ሚሊየን መብለጡ ተገለጸ፡፡

ምንም እንኳን አፍሪካ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመግታት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገች ቢሆንም በአህጉሪቱ 8 ሚሊየን 804 ሺህ 66 ሰዎች በወረርሽኙ እንደተጠቁና የ224 ሺህ 417 ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ነው የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ሪፖርት ያመላከተው፡፡

ከአፍሪካ ሀገራትም ደቡብ አፍሪካ በወረርሽኙ በከፍተኛ ደረጃ እንደተመታችና 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ እንደተጠቁባት እንዲሁም የ90 ሺህ 66 ሰዎች ሕይወት ደግሞ እንዳለፈ ነው በሪፖርቱ የተመላከተው፡፡

ደቡብ አፍሪካ ላይ የተመዘገበው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በአህጉሪቱ ከተመዘገበው 32 ነጥብ 6 በመቶ ያህሉን ሸፍኗልም ነው የተባለው፡፡

በደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ በአፍሪካ ከተመዘገበው 40 ነጥብ 13 በመቶ ያህሉን ይዟል፡፡

ከደቡብ አፍሪካ ቀጥላ ከፍተኛውን የቫይረስ ስርጭት ቁጥር ያስመዘገበችው ሞሮኮ ስትሆን 951 ሺህ 92 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፤ በ3ኛ ደረጃ ከፍተኛ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች የተመዘገቡባት ደግሞ ቱኒዚያ ስትሆን 719 ሺህ 6 ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ነው ሲጂቲ ኤን ያመላከተው፡፡

አዲሱ የ”ኦሚክሮን” ቫይረስ በአህጉሪቷ እንዳይስፋፋ ከፍተኛ ጥንቃቄ እየተደረገ ሲሆን በዓለማችን ላይ ወደ 60 ሀገራት በቫይረሱ መጠቃታቸው ነው የተነገረው፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.