Fana: At a Speed of Life!

በኮሮና ቫይረስ ስጋት ልምምዱን ቤት ውስጥ ያደረገው አትሌት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) መነሻውን ከወደ ቻይና ውሃን ግዛት ያደረገው የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ከሆነ ውሎ አድሯል።

ከቫይረሱ ስርጭት ጋር በተያያዘ አወንታዊ መረጃዎች ቢሰሙም በርካቶች ግን አሁንም በስጋት ላይ ናቸው።

የቫይረሱን ስርጭት በመፍራት ከወደ ቻይና የተሰማው ዜና ደግሞ መነጋገሪያ ሆኗል።

ቻይናዊው የማራቶን ተወዳዳሪ ቫይረሱን በመፍራት ለቀጣዩ ውድድር መኖሪያ ቤት ውስጥ ልምምድ ማድረጉ የበርካቶች መነጋገሪያ አድርጎታል።

ግለሰቡ ለበርካታ ቀናት ከቤቱ እንደማይወጣ ገልጿል፤ ለዚህ ደግሞ በሃገሩ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት መሆኑን ያስረዳል።

ፓን የተባለው የማራቶን ተወዳዳሪ በሚኖርበት አፓርታማ ውስጥ በአነስተኛ ቦታ ልምምዱን እያደረገ ሲሆን፥ እስካሁን 50 ኪሎ ሜትር ያክል መሸፈን መቻሉን ገልጿል።

ርቀቱንም በ4 ሰዓት ከ48 ደቂቃ ከ44 ሰከንድ አጠናቅቄያለሁ ነው ያለው አትሌቱ።

ቤት ውስጥ ልምምድ በሚያደርግበት ወቅትም ጎረቤቶቹ በኮቴ ድምጽ እንዳይረበሹ ጥንቃቄ ማድረጉንም አስረድቷል።

ይህም ቢሆን ግን ከጎረቤቶቹ አሁንም ተቃውሞ አላጣውም፤ ሁኔታው አስጊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከእነ ችግሩ ልምምዱን ቤት ውስጥ ብቻ እንደሚከውንም ተናግሯል።

ምንጭ፦ ኦዲቲ ሴንትራል

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.