Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ምደባና ሹመቶች በህገ-ደንቡ መሠረት መከናወናቸውን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7 2017 (ኤፍ ) የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነምግባር ኮሚሽን የተሰጡ ምደባና ሹመቶች በህገደንቡ መሠረት መከናወናቸውን ገለጸ።

 የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነምግባር ኮሚሽን ሥራ አስፈጻሚ ያካሄደውን 9 መደበኛ ስብሰባው አስመልክተው የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሠላማዊት ዳዊት መግለጫ ሰጥተዋል። 

 በመግለጫቸውም፤ የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነምግባር ኮሚሽን ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ የሚለውን መርህ ከግብ ለማድረስ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

 ኮሚሽኑ 2017 በጀት ዓመትጠንካራ ኢንስፔክሽን፤ ለጠንካራ ፓርቲበሚል በጀመረው ንቅናቄ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

 የአሰራር መመሪያዎችን በማዘጋጀት ስራውን በውጤታማነት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው÷ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የአፈጻጸም መሻሻል መታየቱን ጠቁመዋል።

 ኮሚሽኑ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በፓርቲ ውስጥ የሚፈጸሙ የምደባና ሹመት እንዲሁም ሌሎች ተግባራት ህገደንቡን መሠረት አድርገው ስለመፈጸማቸው ክትትል ማድረጉን ተናግረዋል።

 ኮሚሽኑ የፓርቲውን ጤናማነት ማስጠበቅ፣ መገምገም፣ ስልጠናዎችን መስጠት እንዲሁም ግንዛቤ የማስጨበጥ ዓላማ ይዞ ስራዎቹን እያከናወነ ይገኛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.