Fana: At a Speed of Life!

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎቹን አስመረቀ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 224 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ ውስጥም 25 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ተብሏል።

በምረቃ መርሃ ግብሩም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አወል ሰይድ(ዶ/ር)፣የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባል እና የኮምቦልቻ ቻ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ሙስጠፋ ጀማል እና የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ ከበደ ግዛው(ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅት አወል ሰይድ (ዶ/ር) ÷ለተመራቂ ተማሪዎች ለማደግ አቋራጭ መንገድ የለምና ሁልጊዜም እራሳችሁን ማሳደግና ማስተማር ላይ አተኩሩ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዩኒቨርሲቲው በ38 ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ተማሪዎቹን እያስተማረ ሲሆን÷ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ በተቋሙ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ችግር ፈቺ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ሰዓት ከ21 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።

በእለኒ ተሰማ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.