በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 615 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኝ ተተከለ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በመላ ሀገሪቱ በተከናወነው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ- ግብር 615 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኝ መተከሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡
በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በአንድ ጀንበር 600 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ ተይዞ ወደ ሥራ መገባቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ሆኖም በዛሬው ዕለት በተደረገው ሰፊ ርብርብ 615 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኝ መትከል መቻሉን ነው የገለጹት፡፡
ስኬታማ በሆነው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለተሳተፉ አካላትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል፡፡