ቀሪውን 5 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ለማስመለስ እየሠራሁ ነው – ንግድ ባንክ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከሲስተም ማሻሻያ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ችግር ያለአግባብ ከተወሰደው ብር ያልተመለሰውን 5 ነጥብ 4 ሚሊየን ለማስመለስ እየሠራሁ ነው አለ፡፡
በወቅቱ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው 801 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር 796 ነጥብ 02 ሚሊየን መመለሱን የባንኩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ቀሪውን 0 ነጥብ 67 በመቶ ወይም 5 ነጥብ 4 ሚሊየን ብርም በአጭር ጊዜ ለማስመለስ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ነው ባንኩ ያስታወቀው፡፡