ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አስመራ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አስመራ ገብተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስመራ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የኤርትራው የማስታወቂ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአስመራ ቆይታቸው ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በሃገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጠናዊ ትብብር ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሬድዋን ሁሴን እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አብረው አቅንተዋል፡፡
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
በወቅቱም ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡
በተጨማሪም የተለያዩ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸውም የሚታወስ ነው፡፡