Fana: At a Speed of Life!

የዲቾቶ-ጋላፊ መገንጠያ- በለሆ የኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የዲቾቶ-ጋላፊ መገንጠያ- በለሆ የኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
መንገዱ 78 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ለግንባታው ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል ነው የተባለው፡፡
በሌላ በኩል የአሰብ መዳረሻ የሆነው የሜሎዶኒ መገንጠያ – ማንዳ- ቡሬ የመንገድ ግንባታ ስራ ተጀምሯል፡፡
ለመንገዱ ግንባታ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግ ታውቋል፡፡
በመንገድ ግንባታ ማስጀመሪያውንና በምረቃ መርሃ ግቡሩ ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ ተገኝተዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.