Fana: At a Speed of Life!

የዲቾቶ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ተርሚናል ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የተገነባውየዲቾቶ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ተርሚናል ግንባታ ተጠናቆ ስራ መጀመሩ ተገለፀ፡፡

ተርሚናሉ በ12 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባ ሲሆን 750 ተሸከርካሪዎችን ማስተናገድ ይችላል ነው የተባለው፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በተገኙበት በይፋ ተከፍቷል፡፡

በዙህ ወቅት የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ተርሚናሉ በኢትዮጵያ ትልቁ የወጪ እና የገቢ የንግድ መስመር በሆነው ኢትዮ-ጁቡቲ መስመር መገንባቱ ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው ብለዋል፡፡

እንዲሁም ተርሚናሉ የጭነት አገልግሎትን ለማሳለጥ ከሚሰጠው ጥቅም ባለፈ ለአካባቢው ሰዎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

በለይኩን ዓለም

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.