የኢትዮ ጅቡቲ መንገድ 3ኛ የመቆጣጠርያ ኬላ ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢትዮ ጅቡቲ መንገድ 3ኛ የመቆጣጠርያ ኬላ ዛሬ አፋር በልሆ ላይ በይፋ ተከፍቷል።
የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ፍሬአለም ሺባባው÷ ኬላውን በቦታው ተገኝተው መርቀው ከፍተዋል።
የኬላው መከፈት በአካባቢው ያለውን ህገወጥ የሰዎች ዝውውርንና ኮትሮባንድን ለመከላከል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተነግሯል ።
በዚሁ ወቅት ወይዘሮ ፍሬዓለም ስራው እንዲሳካ ጥረት ላደረጉ ሠራተኞችና አመራሮች የጅቡቲን መንግስት ጨምሮ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።