Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የመንገድ ዳር መብራቶችን የማዘመን ስራ እያከናወነ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ መንገዶች ላይ ያሉትን የመንገድ ዳር መብራቶች በኤል.ኢ.ዲ የመብራት አምፖሎች በመቀየር የማዘመን ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የምሽት የተሽከርካሪ እና የእግረኛ እንቅስቃሴን ምቹ እና ከአደጋ የፀዳ ለማድረግ አዳዲስ የመንገድ ዳር መብራቶችን የመትከል፣ በተለያየ ምክንያት ለብልሽት የተዳረጉትን የመጠገን ስራዎችን ከማከናወን በተጨማሪ የመንገድ ዳር መብራቶችን በማዘመን በኤል.ኢ.ዲ የመቀየር ስራ ሲያከናውን መቆየቱም ነው የተገለጸው፡፡
እነዚህ የኤል.ኢ.ዲ የመንገድ ዳር መብራቶች ከዚህ ቀደም የነበረውን ደብዛዛ ብርሀን ተፈጥሮአዊ በሆነው ነጭ ብርሀን በመተካት የከተማዋን የምሽት የትራፊክ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ፣ ለከተማዋ ድምቀት የሚሰጡ ናቸው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ከአየር ብክለትም ነፃ ከመሆናቸው ባሻገር እስከ 10 ዓመት ድረስ የሚቆይ የአገልግሎት ዘመን ይኖራቸዋልም ነው የተባለው፡፡
በተጨማሪም ከመንገድ ዳር መብራት ጥገና ጋር በተያያዘ በተሽከርካሪ አደጋ ግጭት ምክንያት ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ምሰሶዎችን በሌላ መተካት’ የተበጣጠሱ የመንገድ መብራት ኬብል መቀየር፣ በረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠት ለብልሽት የተዳረጉትን የመጠገን እና ሌሎች ተዛማጅ ስራዎች መከናወኑ ተገልጿል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተያዘው በጀት ዓመት 11ሺህ የመንገድ ዳር መብራት ጥገና ስራዎች ለማከናወን በዕቅድ የያዘ ሲሆን÷ በአምስት ወራት ውስጥ 5 ሺህ 875 አጠቃላይ የጥገና ስራዎችን አከናውኗል ይህም አፈፃፀሙን 53 በመቶ መድረሱን ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.