የአንድነት ፓርክ መካነ-እንስሳት ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ
አዲስ አበባ፣መጋቢት 1፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአንድነት ፓርክ መካነ-እንስሳት ከዛሬ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጓል፡፡
የአንድነት መካነ-እንስሳት በውስጡ 37 አጥቢ እንስሳት እና የአእዋፍት ዝርያዎችን ለመሰብሰብ ታቅዶ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅትም ቀጭኔዎች፣ ነጭ አናብስት ፣ ተኩላዎች፣ ሰጎኖች፣ ማርካት፣ ሳላዎች፣ የሜዳ አህያዎች፣ የቆላ አጋዘን፣ ውድንቢ፣ የቶራ ፈረሶች እና ሌሎች እንስሳት ወደ መካነ እንስሳቱ ገብተው ለጎብኚዎች ክፍት ሆነዋል፡፡
በቅርቡም አቦሸማኔዎች፣ ነጭ አውራሪስ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ እና ሌሎች አጥቢ እንስሳት፣ የጦጣ ዝርያዎች እና አእዋፍት ወደ መካነ እንስሳቱ የሚገቡ መሆኑን ከአንድነት ፓርክ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ጎብኚዎች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ፓርኩ በመምጣት ከሌሎች የጉብኝት መዳረሻዎች በተጨማሪ መካነ-እንስሳቱን መጎብኘት እንደሚችሉም ተገልጿል።