Fana: At a Speed of Life!

ቲክቶክ የትራምፕ እገዳ ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወስድ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)ቲክቶክ የዶናልድ ትራምፕ እገዳ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ፡፡

የቻይናው ተንቀሳቃሽ ምስል አጋሪ ቲክቶክ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኩባንያው በአሜሪካ እንዳይሰራ የጣሉትን እገዳ ለመቃወም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቁ ተነግሯል፡፡

የትራምፕ እገዳ ከቲክቶክ ባለቤት ባይስ ዳንስ ጋር የሚደረግ ግብይትን ከመስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ ይከለክላል፡፡

በዋሽንግተን የሚገኙ ባለስልጣናትም ኩባንያው በአሜሪካ ተጠቃሚዎች በኩል መረጃዎችን ለቻይና መንግስት ሊያስተላልፍ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው ፡፡

በዚህም የኩባንያው ቃል አቀባይ የህግ የበላይነት ወደ ጎን አይባልም ለዚህም የፕሬዝዳንቱን ትዕዛዝ ለመቃወም ወደ ፍርድ ቤት እናመራለን ብለዋል፡፡

የቲክቶክ ህጋዊ እርምጃም በዚህ ሳምንት እንደሚጀምር ይጠብቃል ነው የተባለው፡፡

አጭር ተንቀሳቃሽ ምስል ማጋሪያ ቲክቶክ በአሜሪካ 80 ሚሊየን ተጠቃሚዎች አሉት ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.