Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 724 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 724 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ጣምያለው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በጤፍ፣ በበርበሬ እና በመድሃኒቶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 724 የንግድ ድርጅቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል።

በክልሉ መሰል ችግሮችን በመከታተል በዘላቂነት ለማስወገድ የሚያስችል ግብረ ሃይል መዋቀሩንም ተናግረዋል።

የተለያዩ ሁኔታዎችን በመጠበቅ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ጠቁመዋል።

በክብረወሰን ኑሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.