Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ፕሬዚዳንት ኪርና ተቀናቃኛቸው ማቻርን ፊት ለፊት አገናኙ

ፕሬዚዳንት ኪርና ተቀናቃኛቸው ማቻር ተገናኙ

0 151

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኢጋድ የወቅቱ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻርን ፊት ለፊት እንዲገናኙ አደረጉ።

የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ግብዣ ነው ወደ አዲስ አበባ የመጡት።

በትናንትናው እለትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያሪዲትና የተቀናቃኝ ቡድን መሪ ዶክተር ሬክ ማቻርን በፅህፈት ቤታቸው ውስጥ ፊት ለፊት አገናኝተው እንዲጨባበጡ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያሪዲትና የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር የእራት ግብዣ ማድረጋቸውም ተሰምቷል።

ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያሪዲትና የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር አዲስ አበባ ውስጥ ሲገናኙ ከሁለት ዓመት በኋላ ይህ የመጀመሪያ ነው።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያሪዲትና የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር በአካል ተገናኝተው እንዲወያዩ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ዛሬ በሚካሄደው የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች ስብሰባ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀ መንበር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ የአባል ሀገሮቹ መሪዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በስብሰባው ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ፕሬዚዳንት ስልቫ ኪርና ሪክ ማቼር ለሰላም ዕድል በመስጠት የህዝባቸውን ስደት፣ ሞት፣ መፈናቀል እና እንግልት ለማስቆም እንዲሰሩ ጥሪ ያቀርቡላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

 

 

Comments
Loading...