Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት እና አቅርቦትን ለማመጣጠን እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት እና አቅርቦትን ለማመጣጠን የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው ይህን ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ ከአጋር ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር መቻሉ፣ ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች እንዲሁም መሰል ተግባራት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እየተገኘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም አሁን ላይ ሀገሪቱ በተሻለ ቁመና ላይ ትገኛለች ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከአበዳሪ ሀገራት ጋር ባደረገችው ስምምነት መሰረት የ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር የዕዳ ክፍያ እፎይታን እንዳገኘች ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

ይህም በውጭ ምንዛሬ ግኝት ስራችን ላይ የበለጠ ውጤት እንዲመዘገብ አድርጎታልም ነው ያሉት፡፡

በሰሎሞን ይታየው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.