Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

News

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በመዲናዋ ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ 4 ነጥብ 1 ሚሊየን ካሬ ሜትር መሬት ውል እንዲቋረጥ ወሰነ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 12፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ1997 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ታጥረው የቆዩ 154 ቦታዎች 4 ሚሊየን 126 ሺህ 423 ካሬ ሜትር መሬት የሊዝ ውላቸው ተቋርጦ ለህዝብ ጥቅም ተመላሽ እንዲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ወሰነ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለረጅም…

ኢሕአፓ ከ40 አመታት በላይ የውጪ አገር ቆይታ በኋላ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 12፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ከ40 አመታት በላይ የውጪ አገር ቆይታ በኋላ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገባ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በውጪ ያሉ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለአገር ግንባታ ወደ አገር እንዲገቡ ጥሪ…

የኦዴፓ አዲሱ አመራር ኢትዮጵያን ወደ ፊት ማራማድ በሚያችል መልኩ የተደራጀ ነው – ዶ/ር አብይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የተማሩ፣ ለመምራት የተዘጋጁና ብቃት ያላቸውን ወጣት አመራሮችን ማምጣቱንና ኢትዮጵያን ወደ ፊት ማራማድ በሚያስችል መልኩ እራሱን ማደራጁን የፓርቲው ሊቀመንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለፁ።…

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ 9ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ባለ9 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) 9ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ። ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በጅማ ሲካሄድ የቆየው ይህ ድርጅታዊ ጉባኤ በቆይታው የፓርቲውን ስያሜ ጨምሮ የአርማ እና የመዝሙር ለውጥ…

ኦዴፓ ዶ/ር አብይን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ለማን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ በድጋሚ መረጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ድርጅታዊ ጉባዔ የፓርቲውን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር መረጠ። ፓርቲው በዛሬው እለት ባካሄደው ምርጫ፦ 1 ዶክተር አብይ አህመድን የፓርቲው ሊቀመንበር 2 አቶ ለማ መገርሳን…

ኦዴፓ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጅማ እየተካሄደ ያለው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ኦዴፓ/  9ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ አካሂዷል። የፓርቲውን ስያሜ ከኦህዴድ ወደ ኦዴፓ የቀየረው ድርጅታዊ ጉባኤ አዲስ አርማ እና መዝሙርንም አፅድቋል። ጉባኤው…

ኦህዴድ ስያሜውን ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ቀየረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ ስያሜውን ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ቀየረ። ፓርቲው ስያሜውን የቀየረው በጅማ እያካሄደ ባለው 9ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ነው። 14 ነባር አመራሮችንም በክብር አሰናብቷል። አቶ አባዱላ ገመዳ…

ኦህዴድ 14 ነባር አመራሮችን በክብር አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስያሜውን ዛሬ ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የቀየረው ኦህዴድ 14 ነባር አመራሮችን በክብር አሰናበተ። ፓርቲው በጅማ እያካሄደ ባለው 9ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ ነው ነባር አመራሮቹን በክብር ያሰናበተው። በዚህም መሰረት፦ አቶ አባዱላ…

በቡራዩ ከተማና አካባቢዋ በተፈፀመ ግድያ፣ የአካል ጉዳትና ዘረፋ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቡራዩ ከተማ እና አካባቢዋ ባሳለፍነው ሳምንት ከተፈፀመው ግድያ፣ የአካልጉዳትና ዘረፋ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ። ተጠርጣሪዎቹ በዛሬው እለት በቡራዩ የወረዳ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ነው የቀረቡት። ፍርድ ቤቱ…

ኢትዮጵያ በጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነቷ ስኬታማ ስራዎችን ማከናዎኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ መስከረም 10፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭንነት አባልነቷ ስኬታማ ስራዎችን ማከናዎኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሀገሪቱ ባለፉት 21 ወራት በጸጥታው ምክር…