Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ከእግርኳስ ሜዳ ስለምለያይበት ጊዜ አስቤ አላውቅም – ሊዮኔል ሜሲ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በአሁኑ ወቅት ለኢንተርሚያሚ እየተጫወተ ይገኛል። ከወራት በኋላ 37ኛ ዓመቱን የሚይዘው ሊዮኔል ሜሲ ከቢግ ታይም ፖድካስት ጋር ባደረገው ቃል ምልልስ፤ የእድሜው መግፋት በእግርኳስ ህይወቱ ላይ የሚያመጣው ጫና እንደሌለ ተናግሯል። በመሆኑም በእግር ኳስ ሜዳ ላይ ስለሚያስመዘግበው ስኬት እንጂ ስለ ዕድሜው አስቦና ተጨንቆ እንደማያውቅ ተናግሯል፡፡ “በእግርኳስ እዝናናለሁ፣ ባለሁበት ቡድን እና በነገሮች ሁሉ ደስተኛ ነኝ፣ አሁን ላይ ስራዬ ላይ ስለማተኮር እንጂ…
Read More...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ እንዳስታወቀው፤ አለልኝ በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ተለይቶ በትውልድ ስፍራው አርባ ምንጭ ለእረፍት የሄደ ሲሆን ትናንት ምሽት በድንገት ህይወቱ አልፏል።…

በአፍሪካ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና በተካሄደው በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል። ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አቀባበል አድርገውለታል።…

በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡ በቻይና ሁዋን ከተማ በተካሄደ የሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት ማሬ ዲባባ ርቀቱን 2 ሰዓት 25 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች፡፡ በተመሳሳይ በጣልያን ሚላኖ ከተማ በተካሄደ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድር…

ኢትዮጵያ ሌሴቶን 2 ለ 1 አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሁለተኛው ዙር የወዳጅነት ጨዋታ ሌሴቶን 2 ለ 1 አሸንፋለች፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው የአቋም መፈተሻ (የወዳጅነት ጨዋታ) ሌሴቶ በመጀመሪያው አጋማሽ ሌህሎሆኖሎ ፎቶአኔ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል እየመራች ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በሁለተኛው አጋማሽ ቸርነት ጉግሳ እና ከነዓን…

በ45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው ቡድን የማጠቃለያ ልምምድ አከናወነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰርቢያ ቤልግሬድ በሚካሄደው 45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው ቡድን የማጠቃለያ ልምምዱን ዛሬ አከናወነ። ከሳምንት በኋላ በፈረንጆቹ መጋቢት 30 ቀን 2024 በሚካሄደው ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የአትሌቲክስ ቡድን ጠንካራ ልምምድ ሲያካሂድ መቆየቱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን…

ኢትዮጵያ የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድርን ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድርን በ18 ሜዳሊያ ናይጄሪያን በመከተል በ2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡ ላለፋት አምስት ቀናት በጋና አክራ ዩንቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየው 13ኛው የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድር ተጠናቋል። በውድድሩ ኢትዮጵያ በ47 ወንድ፣ በ40 ሴት በድምሩ…