Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በማንዴላ መታሰቢያ ውድድር ውጤት ላስመዘገበው ቡድን አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ የማንዴላ መታስቢያ ውድድር ላይ በመሳተፍ ውጤት ያስመዘገበው የኢትዮጵያ ቦክስ ብሔራዊ ቡድን ወደ ሀገሩ ሲመለስ አቀባበል ተደረገለት። ቡድኑ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ ቢልልኝ መቆያ እንዲሁም የቦክስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ በውድድሩ ላይ በ 54 ኪ/ግ በሱራፌል አላዩ፣ በ60 ኪ/ግ በሚሊዩን…
Read More...

ኢትዮጵያ በማንዴላ ዋንጫ የአፍሪካ ቦክስ ውድድር ባስመዘገበችው ድል ኤምባሲው ደስታውን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በማንዴላ ዋንጫ የአፍሪካ ቦክስ ውድድር ባስመዘገበችው ድል በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደስታውን ገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ በደርባን በተካሄደው የቦክስ ውድድር ላይ ሦስት የብር እና ሦስት የነሐስ በድምሩ ስድስት ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) ሁሉንም ተወዳዳሪዎችና የልዑካን ቡድን አመራሮች…

 በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከተማ ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ባህርዳር ከተማ ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ቸርነት ጉግሳ ሁለቱንም የባህርዳር ከተማ ግቦች በፍጹም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር÷ የወልቂጤን ብቸኛ ግብ ደግሞ ፉዓድ አብደላ አስቆጥሯል፡፡ በውጤቱ መሰረትም የጣና ሞገዶቹ…

በማንዴላ ዋንጫ የአፍሪካ ቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ 6 ሜዳሊያ በመሰብሰብ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማንዴላ አፍሪካ ቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ ሶስት ብርና ሶስት የነሐስ በአጠቃላይ ስድስት ሜዳልያ በማግኘት ውድድሩን አጠናቃለች። በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያ በሱራፌል አላዩ፣ ሚሊዮን ጨፎ እና ቤተል ወልዱ የነሃስ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ ቤተልሄም ገዛህኝ፣ ሮማን አሰፋ እና ተመስገን ምትኩ ደግሞ…

ማንቼስተር ዩናይትድ እና ማንቼስተር ሲቲ ለዋንጫ ይፋለማሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ እና ማንቼስተር ሲቲ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ለማንሳት ይፋለማሉ፡፡ ማንቼስተር ዩናይትድና ኮቬንትሪ ሲቲ ዛሬ ያደረጉት ጨዋታ መደበኛና በጭማሪ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 3 አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት አምርተዋል፡፡ በዚህም ዩናይትድ በመለያ ምት 4 ለ 2 በማሸነፍ ለዋንጫው መፋለም የሚያስችለውን ድል…

ሊቨርፑል ፉልሃምን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፉልሃምን የገጠመው ሊቨርፑል 3ለ 1 አሸንፏል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው አጋማሽ አንድ አቻ ሆነው ወደ መልበሻ ክፍል ቢያመሩም ከዕረፍት መልስ ሊቨርፑል ባስቆጠራቸው 2 ጎሎች ፉልሃም ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎም በ74 ነጥብ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር እኩል…

ኤቨርተን፣ ክሪስታል ፓላስ እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄዱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ኤቨርተን፣ ክሪስታል ፓላስ እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ በዚህም ኤቨርተን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ ክሪስታል ፓላስ ዌስትሃምን 5 ለ 2 ረትቷል፡፡ እንዲሁም ከመመራት ተነስቶ አስቶንቪላ ቦርንማውዝን 3 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል፡፡