Fana: At a Speed of Life!

ለሁሉም የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጥሪ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 02፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሁሉም የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጥሪ አድረገ። ለአምባሳደሮቹ ጥሪ የተደረገው በተለያዩ ወቅታዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ሊደረግ መሆኑን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። አምባሳደሮቹ…

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በአቶ ገላሳ ዲልቦ ከሚመራው የኦነግ አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 02፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በአቶ ገላሳ ዲልቦ ከሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ጋር ተወያይተዋል። በአቶ ገላሳ ዲልቦ የሚመራው የኦነግ የአመራር ቡድን መንግስት ያደረገለትን ጥሪ ተከትሎ ነው ባሳለፍነው…

በፖለቲካ ፓርቲዎችና ድርጅቶች መካከል ለሚደረገው ውይይትና ድርድር 32 አጀንዳዎች ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፖለቲካ ፓርቲዎች እና ድርጅቶች መካከል ለሚደረገው ውይይት እና ድርድር 32 አጀንዳዎች ቀርበዋል። በፖለቲካ ፓርቲዎች እና ድርጅቶች በቀጣይ በሚደረገው ውይይት እና ድርድር ዙሪያ ከምርጫ ቦርድ ጋር በዛሬው እለት ተወያይተዋል።…

የታራሚዎች ሰብአዊ መብት አያያዝ ለውጥ ማሳየቱን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 02፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት የታራሚዎች ሰብአዊ መብት አያያዝ ለውጥ ማሳየቱን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ። ተቋሙ የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀሙን በማስመልከት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል። የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ዋና…

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመንግስት ተቋማት መዘጋት ዙሪያ ሲደረግ የነበረውን ስብሰባ ረግጠው ወጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 02፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በከፊል በተዘጉ የመንግስት ተቋማት ዙሪያ ከዴሞክራቲክ መሪዎች ጋር ሲያደርጉ የነበረውን ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸው ተነግሯል። የሪፐብሊካኑ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስብሰባውን ረግጠው የወጡት የዴሞክራቶቹ ናንሲ…

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ለከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚዎች ዋስትና ለመግባት መዘጋጀቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 02፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ለሚሰጣቸው ከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚዎች ዋስትና ለመግባት መዘጋጀቱን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ከከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ደንበኞቹ ጋር በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በዛሬው እለት ውይይት አድርጓል።…

አይፎን ስልክ ለመግዛት ኩላሊቱን የሸጠው ቻይናዊ የእድሜ ልክ አካል ጉዳተኛ ሆኗል

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዠያዎ ዋንግ የተባለው ቻይናዊ እድሜው የ17 ዓመት ታዳጊ ወጣት እያለ ነበር አይፎን 4 የተባለውን ስማርት ስልክ ለመግዛት አንድ ኩላሊቱን ለመሸጥ የወሰነው። በወቅቱም ከደሃ ቤተሰብ የተወለደው እና ስልኩን ለመግዛት በቂ ገንዘብ የሌለው ዋንግ አንድ…

ትንፋሻችንን በመለካት ምን መመገብ እንዳለበን የሚነግረን መሳሪያ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትንፋሻችንን በመለካት ምን አይነት ምግብ መመገብ እንዳለብን የሚጠቁሙን ሁለት መሳሪያዎች ለእይታ ቀርበዋል። አነስተኛ መጠን ያላቸው እነዚህ የቴክኖለጂ ፈጠራዎች በአሜሪካዋ ላስ ቬጋስ በተካሄደ አውደ ርእይ ላይ ለእይታ መቅረባቸውም ተነግሯል።…

በቻይና በሌሊት ወፍ ላይ ከኢቦላ ጋር የሚመሳሰል ቫይረስ መገኘቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 01፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና ከኢቦላ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ቫይረስ በሌሊት ወፍ ላይ መገኘቱ ጥናት አመለከተ። “መንገላ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ቫይረሱ አደገኛ ነው የተባለ ሲሆን፥ በቻይና ዩዋን ግዛት የሌሊት ወፍ ላይ መገኘቱ ነው በጥናቱ የተገለፀው። ቫይረሱም…

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካራን ጋር ተወያዩ። መሪዎቹ በውይይታቸው የሃገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል። አሁን ላይ በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለውን…