Fana: At a Speed of Life!

በአልጀሪያ ሆስፒታል ውስጥ በተነሳ እሳት 8 ህጻናት ሞቱ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጀሪያ ሆስፒታል ውስጥ በተነሳ እሳት 8 ህጻናት መሞታቸው ተነገረ። አደጋው በምስራቃዊ የሃገሪቱ ክፍል በሚገኝ ሆስፒታል የህጻናት ክፍል ውስጥ የተነሳ ነው ተብሏል። ከአደጋው 11 ህጻናትን መታደግ መቻሉን የሆስፒታሉ ቃል አቀባይ…

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ። ውይይቱ ከኒውዮርኩ የተመድ 74ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን የተካሄደ ነው። ፕሬዚዳንቷ በዚህ ወቅት ባለፈው አንድ አመት በኢትዮጵያ…

ሊዮኔል ሜሲ የፊፋ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የባርሴሎናው አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል። ሜሲ ትናንት ምሽት በጣሊያን ሚላን በተካሄደው የሽልማት ስነ ስርዓት ቨርጂል ቫንዳይክን እና ክርስቲያኖ ሮናልዶን…

የዜጎችን ጥራት ያለው የጤና እንክብካቤ የማግኘት መብት ለማስጠበቅ እየተሰራ ነው – ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ ዜጎች ጥራት ያለው የጤና እንክብካቤ የማግኘት መብታቸው እንዲጠበቅ እየሰራች መሆኗን ተናገሩ። በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን…

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሃል ክፍል የአርማታ ሙሌት ስራ ተጀምሯል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሃል ክፍል የአርማታ ሙሌት ስራ መጀመሩን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አብርሃም በላይ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ…

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከኦሮሚያ ት/ት ቢሮ የምስክር ወረቀት እና የትምህርት ልማት አጋርነት ሽልማት ተበረከተላቸው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የምስክር ወረቀት እና የትምህርት ልማት አጋርነት ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡ ለቀዳማዊት እመቤቷ ከኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ የተበረከተላቸውን የምስክር ወረቀት እና ሽልማት የቀዳማዊት…

በደምበጫ ዙሪያ ወረዳ በትራፊክ አደጋ 16 ሰዎች ሞቱ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ሕይወት አለፈ። አደጋው በዛሬው እለት ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ የጨረቃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ የጭነት አይሱዙ ሁለት መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻዎችንና አንድ ባጃጅ…

የቴሌኮም አገልግሎት ወርሃዊ ክፍያን በባንከ መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቴሌኮም አገልግሎት ወርሃዊ ክፍያን በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይዎት ታምሩ እና የኢትዮጵያ ንግድ…