Fana: At a Speed of Life!

የጥቁር ገበያ ምንዛሬ ኢትዮጵያን የማዳከም ዘመቻ አካል መሆኑን ተገንዝበን ህጋዊ አማራጭ ልንጠቀም ይገባል – አቶ አቤ ሳኖ

አዲስ አበባ፣ህዳር 26፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥቁር ገበያ ምንዛሬ ኢትዮጵያን የማዳከም ዘመቻ አካል በመሆኑ “ህጋዊ የምንዛሬ አማራጮችን ብቻ መጠቀም ይገባል” ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ፡፡

አቶ አቤ ሳኖ፤ በህገ-ወጥ መንገድ የሚመነዘር የውጭ አገር ገንዘብ በአመዛኙ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለሚሰሩ ኃይሎች እንደሚውል ነው የተናገሩት፡፡

ይህም ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ የማዳከም ዘመቻ አካል መሆኑን ጠቅሰው፤ ድርጊቱ በሁለት መልኩ አገርን እንደሚጎዳ አብራርተዋል፡፡

በአንድ በኩል ጦርነት ከፍተው አገር እየወጉ የሚገኙ የውስጥ ጠላቶችን አቅም ለማጎልበት የሚውል ሲሆን÷በሌላ በኩል ደግሞ ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ውጭ አገር እንዲሸሽ በማድረግ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ እንደሚያደርግ ነው የገለጹት፡፡

በዚህም የውጭ አገር ገንዘብን በጥቁር ገበያ መመንዘር ለጥቂት የገንዘብ ጭማሪ ሲባል አገርን የሚጎዱ ኃይሎችን መተባበር መሆኑን መገንዘብ ይገባል ነው ያሉት፡፡

በመሆኑም በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ገንዘብን በህጋዊ መንገድ ብቻ በመመንዘር የኢትዮጵያን ህልውና ለመጠበቅ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወደ አገር ውስጥ ከሚላከው የውጭ አገር ገንዘብ መካከል በህጋዊ መንገድ የሚመነዘረው ከ30 በመቶ እንደማይበልጥ ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.