Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በሁለት ክፍለ-ከተሞች በ5 ሰዎች ላይ የኮሌራ ወረርሽኝ ምልክት ታየ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ በአቃቂና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች በ5 ሰዎች ላይ የኮሌራ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት /አተት/ ምልክት ታይቶባቸው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቋል። ኢንስቲትዩቱ ለፋና…

ተመድ በሶማሊያ ያለውን የሰላም አስከባሪ ኃይል ቁጥር ሊቀንስ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በሶማሊያ የተሰማራውን የሰላም አስከባሪ ኃይል ቁጥር ለመቀነስ ውሳኔ አሳላፈ። ተመድ በትናትናው ዕለት በሶማሊያ የሚገኘውን የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል /አሚሶም/ን በ1000 ለመቀነስ…

በጎንደር ከተማ የሰላም ውይይት ተካሂደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጎንደር እና አካባቢዋ ተነስተው የነበሩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሰላም ውይይት በጎንደር ከተማ ተካሄደ። በውይይቱ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ምሁራን፣ የ33ኛ እና የ31ኛ ክፈለ ጦር…

ሆዜ አንቶኒዮ ሬይስ በደረሰበት የመኪና አደጋ ህይወቱ አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀድሞ የአርሰናል የሪያል ማድሪድ ተጫዋች የነበረው ሆዜ አንቶኒዮ ሬይስ በመኪና አደጋ ህይወቱ አለፈ። የ35 ዓመቱ ሆዜ አንቶኒዮ ሬይስ ህልፈት የተሰማው ከደቂቃዎች በፊት ነው። ሬይስ የመጀመሪያውን ጨዋታ ያደረገው ገና በ16 ዓመቱ በስፔኑ…

የደቡብ ክልል የባህል ፌስቲቫል በወላይታ ሶዶ ዛሬ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 4ኛው የደቡብ ክልል የባህል ፌስቲቫል በወላይታ ሶዶ ከተማ በድምቀት ዛሬ ተጀመረ። ፌስቲቫሉ ፟፟፟“ባህላችን ለሰላማችንና አንድነታችን” በሚል መሪ ቃል በወላይታ ሶዶ ከተማ ከ15 ሺህ በላይ ታዳሚዎች በተሳተፉበት በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት…

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቦሪስ ጆንሰን ቴሬዛ ሜይን መተካት የሚችሉ ምርጡ ሰው ናቸው አሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ የሆኑትን ቴሬዛ ሜይን ለመተካት ቦሪስ ጆንሰን ሁነኛ አማራጭ ናቸው አሉ። በብሪታኒያ ጉብኝት ለማድረግ እየተዘጋጁ የሚገኙት ትራመፕ የቀድሞው…

የሰላም ሚንስቴር የተፈናቀሉ ዜጎች እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ ወደ ቀያቸው ለመመለስ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ ወደ ቀያቸው በመመለስ በዘላቂነት ለማቋቋም እየሰራ መሆኑን የሰላም ሚንስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል አስታወቁ። የሰላም ሚኒስትሯ ዛሬ በሰጡት መግለጫ…

የአዴፓ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የውይይት መድረክ በባህር ዳር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የውይይት መድረክ በዛሬው እለት በባህር ዳር ከተማ ተጀምራል። መድረኩን የአዴፓ ሊቀመንበር እና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በንግግር ከፍተውታል። አቶ…

በመዲናዋ በኦዲት ግኝት ሪፖርት አስተያየት ላይ እርምጃ ወስደው ያላሳወቁ ተቋማት ላይ ክስ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ በኦዲት ግኝት ሪፖርት አስተያየት ላይ እርምጃ ወስደው ያላሳወቁ ተቋማት ላይ ክስ ተመሰረተ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ከ2003 እስከ 2011 ግማሽ በጀት ዓመት ከመመሪያ ውጭ ግዢ የፈጸሙ ተቋማትን በመለየት ተቋማቱ…

ሰሜን ኮሪያ የኪምና ትራምፕ ውይይት ያለስኬት በመጠናቀቁ ከፍተኛ ዲፕሎማቷን ገደለች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰሜን ኮሪያ የኪምና የዶናልድ ትራምፕ ውይይት ያለስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ ከፍተኛ ዲፕሎማቷን መግደሏ ተሰማ። የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጁንግ ኡን እና የአሜሪካው አቻቸው የመጀመሪያ ውይታቸውን ሲንጋፖር ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። የመሪዎቹ…