Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

በጋዛ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ምግብና ሌሎች ድጋፎችን ማድረስ እንዳልተቻለ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት የተነሳ በጋዛ የግንኙነት መሥመር ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ምግብና ሌሎች የሰብዓዊ አቅርቦቶችን ወደ ሥፍራው ማድረስ እንዳልቻሉ ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች ተናገሩ፡፡ ድርጅቶቹ የሚሠጡትን አገልግሎት በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ…

የማላዊ ፕሬዚዳንት በራሳቸውና ካቢኔያቸው ላይ የውጪ ሀገራት ጉዞ እገዳ ጣሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማላዊ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ (ዶ/ር) በራሳቸው እና ካቢኔያቸው ላይ የውጭ ሀገራት ጉዞ እገዳ መጣላቸው ተሰምቷል፡፡ የጉዞ እገዳው የሀገሪቱ ገንዘብ የመግዛት አቅም 44 በመቶ መዳከሙን ተከትሎ የውጭ ምንዛሬን ለማዳን ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡…

አሜሪካና ቻይና ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እና ቻይና ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል መስማማታቸው ተነገረ፡፡ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በሳን ፍራንሲስኮ የባህር ወሽመጥ አካባቢ ከቻይና ፕሬዚደንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡ ይህም በዓመታት ውስጥ “በጣም…

ናሬንድራ ሞዲ ለአርሶ አደሮች የ2 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 6 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ምርጫ መቃረቡን ተከትሎ ለአርሶ አደሮች የ2 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርገዋል፡፡ ድጋፉ በሀገሪቱ 80 ሚሊየን የሚደርሱ አርሶ አደሮችን ለመርዳት የተዘጋጀው የበጎ አድራጎት መርሐ ግብር አካል መሆኑ…

ሞሮኮ ለመጀመያ ጊዜ በሀገር ውስጥ የተሰራውን መኪና ለሽያጭ አቀረበች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሞሮኮ ኒኦ ሞተርስ በተባለው የሀገር ውስጥ መኪና አምራች ኩባንያ የተገጣጠመውን መኪና ለሽያጭ አቅርባለች፡፡ በተያዘው ወር ይፋ የሆነው ይህ መኪና ከደቡብ አፍሪካው ሪኖልት መኪና እና ከቻይና የመኪና ብራንዶች ጋር ይወዳደራል ነው የተባለው፡፡…

ኬንያ በዓመት 20 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ለማስገባት ማቀዷ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያ በነዳጅ ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስ በየዓመቱ 20 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ከውጭ ለማስገባት ማቀዷ ተገለጸ፡፡ ኬንያ ዕቅዱን ያወጣችው በሀገሪቷ እያደገ የመጣውን የተሽከርካሪ ግዢ ፍላጎት ለማሟላትና የነዳጅ ፍጆታዋን በዘላቂነት…

ቻይና እና አሜሪካ የዓየር ንብረት ለውጥ ቀውስን ለመፍታት በትብብር ሊሠሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና እና አሜሪካ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የዓየር ንብረት ለውጥ ቀውስ በትብብር ለመፍታት እንደሚሠሩ ገለጹ፡፡ ሀገራቱ ትብብራቸውን ለማሳደግ መስማማታቸውንና የጋራ መግለጫ ማውጣታቸውን የቻይና የሥነ-ምኅዳር እና የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር በዛሬው…

እስራዔል ከሃማስ ጋር እየተደራደረች መሆኑ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራዔል ከሃማስ ጋር የታገቱባትን ንጹሐን ለማስለቀቅ እየተደራደረች መሆኑ ተገለጸ፡፡ አሁን ላይ ሁለቱ አካላት ጦርነቱን ማካሄድ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ የያዟቸውን ንጹሃን ለመለዋወጥ መቃረባቸውም ነው የተገለጸው። ድርድሩ ከተሳካ በፍልስጤም ታጣቂ…

የአውሮፓ ኅብረት ለዩክሬን ካለፈው ዓመት ጀምሮ የ27 ቢሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉ ተሰማ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን ካለፈው አመት ጀምሮ የ27 ቢሊየን ዩሮ ወታደራዊ ድጋፍ ማድረጉን የህብረቱ የውጭ ጉዳይና ፀጥታ ሃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ገለጹ። ቦሬል በቤልጂየም ብራሰልስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አባል ሀገራቱ ካለፈው አመት ጀምሮ ለኪየቭ…

ኔፓል ቲክቶክን ልታግድ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኔፓል በህብረተሰቡ ማኅበራዊ መሥተጋብር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ያለችውን ‘ቲክቶክ’ የማህበራዊ ትሥሥር ገፅ አማራጭ ልታግድ መሆኗ ተሰማ፡፡ እንደ ገልፍ ቱዴይ ዘገባ፤ ኔፓል የቻይናውን ታዋቂ የማኅበራዊ ትሥሥር ገፅ በይፋ ልታግድ መሆኗን…