Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፕሬዚዳንት ፑቱን የሩሲያ ወታደራዊ ሀይል የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ወታደራዊ ሀይል ከጠላት ሊሰነዘር የሚችልን ጥቃት ለመመከት በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለፁ፡፡ ሩሲያ በናዚ ላይ ድል የተቀዳጀችበትን 79ኛ ዓመት በተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶች በሞስኮ ከተማ አክብራለች፡፡…

ሩሲያ ከሴራሊዮን ጋር በኒውኩሌር ኃይል ዙሪያ በትብብር ለመስራት ማሰቧን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ከሴራሊዮን ጋር በኒውኩሌር ኃይል ዙሪያ በትብብር ለመስራት ማሰቧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ገልጸዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በትናንትናው ዕለት ከሴራሊዮን አቻቸው ቲሞቲ ሙሳ ካባ ጋር ተገናኝተው መክረዋል። ኒውኩሌር ኃይል…

በአፍሪካ የአፈር ማዳበሪያ ምርትን ለማሳደግ 15 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የአፈር ማዳበሪያ ምርትን ለማሳደግ 15 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ገለፀ፡፡ ከትናንት ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የአፈር ማዳበሪያ እና የአፈር ጤና ጉባኤ ላይ÷ በአፈር ማዳበሪያ ፖሊሲ፣ ጥናት እና ልማት…

በደቡብ አፍሪካ ከተደረመሰ ሕንፃ ውስጥ 11 ሰራተኞች በህይወት ተገኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ከተደረመሰ ሕንፃ ውስጥ 11 ሰራተኞች በህይወት መገኘታቸው ተሰምቷል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ጆርጅ ከተማ በግንባታ ቦታ ላይ የነበረ ግዙፍ ፎቅ ሕንጻ የተደረመሰ ሲሆን ፥ 75 ሰዎች እዚያ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡ በዚህ ፍለጋም…

በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ኬንያውያን አስቸኳይ ድጋፍ ሊቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ በናይሮቢ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው እያንዳንዱ ቤተሰብ የአስቸይ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያቀርቡ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ገለጹ፡፡ ፕሬዚዳንቱ የጎርፍ አደጋ የደረሰባቸውን አካባቢዎች የጎበኙ ሲሆን በዚሁ…

ሃማስ የቀረበውን የተኩስ አቁም ስምምነት ሃሳብ ተቀብያለሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃማስ በግብጽ እና ኳታር የቀረበውን የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት የውሳኔ ሃሳብ መቀበሉን አስታውቋል። ውሳኔው የእስራኤል ጦር በምሥራቅ ራፋህ የሚገኙ 100 ሺህ በላይ ዜጎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቡን ተከትሎ የተወሰነ ነው ተብሏል፡፡…

ፑቲን ታክቲካል የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልምምድ እንዲደረግ ትዕዛዝ ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታክቲካል (ስልታዊ) የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልምምድ እንዲደረግ ለሀገሪቱ ጦር ትዕዛዝ መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡ ልምምዱ አንዳንድ ምዕራባውያን ባለስልጣናት የሚሰነዘሩትን ጠብ አጫሪ መግለጫ እና ዛቻ ተከትሎ…

እስራኤል በምሥራቅ ራፋህ የተጠለሉ ጋዛውያን እንዲወጡ አሳሰበች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ ራፋህ የተጠለሉ ጋዛውያን አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የእስራኤል ጦር አሳሰበ፡፡ በአካባቢው ውጥረት የነገሰው በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነትን ለማስፈን እና ታጋቾችን ለማስፈታት ያለሙ ንግግሮች ሊቋረጡ መሆናቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡…

በቻይና በአውራ ጎዳና መደርመስ የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ለቀናት የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በጉዋንግዶንግ ግዛት በአውራ ጎዳና ላይ በደረሰ የመደርመስ አደጋ የ19 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሌሎች 30 ሰዎች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው…

በኮሎምቢያ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜናዊ ኮሎምቢያ ገጠራማ ስፍራ ላይ በተከሰተ የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡ የኮሎምቢያ ጦር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው÷ ሄሎኮፕተሯ በሰሜናዊ ኮሎምቢያ የሽምቅ ተዋጊዎችን እና የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎችን…