Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
የ18 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው የአውሮፕላን አደጋ አብራሪው በሕይወት ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኔፓል ዋና ከተማ ካትማንዱ በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ አብራሪው በሕይወት ሲገኝ የ18 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡
በርካቶችን ከቀጠፈው ከዚህ አደጋ በሕይወት የተገኘው የአውሮፕላኑ አብራሪም በአሁኑ ወቅት የሕክምና ክትትል እየተደረገለት መሆኑ…
ካማላ ሃሪስ ለምርጫ ቅስቀሳ በ24 ሰዓት 81 ሚሊየን ዶላር አሰባሰቡ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባይደን ምክትላቸውን በመተካት እራሳቸውን ከተወዳዳሪነት ባገለሉ ማግስት ካማላ ሃሪስ ባደረጉት ዘመቻ በ24 ሰዓት ውስጥ 81 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አሰባስበዋል፡፡
በድጋፍ አሰባሰቡ ላይም ከ8 ሚሊየን 88 ሺህ በላይ መደበኛ…
ኅብረቱ እና ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ልማት የዓረብ ባንክ ለአኅጉሪቱ ዕድገት በጋራ እንደሚሠሩ አስታወቁ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ኅብረት እና ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ልማት የዓረብ ባንክ ለአኅጉሪቱ ዕድገት በአጋርነት እንደሚሠሩ አስታውቀዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት የግማሽ ዓመት ግምገማ ጉባዔ በጋና አክራ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ከጉባዔው ጎን ለጎንም የአፍሪካ ኅብረት…
ሩሲያ 75 የዩክሬን ድሮኖችን ማውደሟን ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ የአየር መከላከያ ዘዴ 75 የዩክሬን ድሮኖችን ማውደሙን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ከ75 ድሮኖች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በሀገሪቱ ደቡብ ምዕራብ በምትገኘው ሮስቶቭ ግዛት ውስጥ መውደማቸውም ተጠቁሟል፡፡
ከዩክሬን…
የአፍሪካ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ውህደት እንዲፋጠን ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የኢኮኖሚያዊ ውህደት እንዲፋጠንና የአህጉሪቱ ዜጎችን ፍላጎት እንዲሳካ ተጠይቋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ከቡድን 20 እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጋር ከመገናኘቱ በፊት በአፍሪካ ውህደት ላይ ለመወያየትና አንድ ወጥ አቋም ለመያዝ…
ከአንድሮይድ አንጻር የአይፎን ስልኮች የመጠለፍ ዕድል ዝቅተኛ ነው – ጥናት
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአንድሮይድ አንጻር አይፎን ስልኮች የመጠለፍ ዕድላቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ሴል ብራይት የተሰኘ የእስራኤል ዲጂታል ኢንተለጀንስ ኩባንያ ጥናት ውጤት አመላከተ፡፡
የአሜሪካ ፀጥታ እና ደኅንነት ተቋም (ኤፍ ቢ አይ) በዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ…
እስራኤል በሁቲ አማጺያን ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በሰሜናዊ የመን በሚንቀሳቀሱ የሁቲ አማጺያን ላይ የተቀናጀ የአየር ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች፡፡
ጥቃቱ አማጺያኑ ቀደም ሲል በቴል-አቪቭ የፈጸሙትን የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ተከትሎ የተወሰደ አጸፋዊ እርምጃ ነው ተብሏል፡፡…
የአይቲ መቋረጥን ተከትሎ ከመረጃ ጠላፊዎች ተጠበቁ የሚሉ ማስጠንቀቂያዎች ከፍ እያሉ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት በዓለም ዙሪያ የጉዞ ቀውስ ያስከተለው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መቆራረጥ አሁንም መጠነኛ መስተጓጎል መፍጠሩን ቀጥሏል።
ይሁንና ክስተቱን ተከትሎ መረጃ መጥለፍ የሚፈልጉ ወንጀለኞች ሊያስከትሉ ከሚችሉት ተጨማሪ አደጋ ራስን መጠበቅ…
አፍሪካ የ15 ሚሊየን መምህራን እጥረት አጋጥሟታል – ኅብረቱ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአኅጉሪቱ የ15 ሚሊየን መምህራን እጥረት ማጋጠሙን የአፍሪካ ኅብረት አስታውቋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት የትምህርት፣ የሣይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር መሐመድ ባልሆሲን በሰጡት መግለጫ፥ የመምህራን እጥረቱ በአኅጉሪቱ አሉታዊ ተጽዕኖ…
በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እክል የተለያዩ ተቋማት ስራቸው መደናቀፉ ተነገረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ባጋጠመ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እክል የተለያዩ አየር መንገዶች፣ ባንኮችና መገናኛ ብዙሃን ስራቸው መደናቀፉን የቢቢሲ ዘገባ አመለከተ።
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እክሉ በተለያዩ አየር መንገዶች በረራ እንዳይካሄድ ያስገደደ ሲሆን፤…