Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡ በክልሉ ግብርና ቢሮ በምግብ ስርዓት…

የአፍሪካ ኢንተርኔት አስተዳደር ኮንፈረንስ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 13ኛው የአፍሪካ ኢንተርኔት አስተዳደር ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። “ዲጂታል አፍሪካን እውን ለማድረግ ጠንካራ ባለድርሻ አካላትን መገንባት ያስፈልጋል” በሚል መሪ ሐሳብም ዛሬ ከፓርላማ አባላት ጋር ወይይት ተደርጓል። በዚሁ…

የዓለም የቱሪዝም ቀን በኦሮሚያ ክልል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የቱሪዝም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ45ኛ ጊዜ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ37ኛ ጊዜ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ ዛሬን ጨምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ይከበራል። ‘’ቱሪዝም ለሰላም’’ በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ አርሲ ዞን…

የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ማዕከላት የማስገባት ሒደት ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ ተዋጊዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ሥራ በነገው ዕለት እንደሚጀምር የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በሰጡት መግለጫ÷ ተቋሙ የተሰጠውን ሀገራዊ…

ዓለም አቀፉ የህፃናት ቀን በመዲናዋ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮ የዓለም ህፃናት ቀን በዓለም ለ35ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል፡፡ ቀኑ "ህፃናት የሚሉት አላቸው እናድምጣቸው!" በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡ በመድረኩ ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ…

አዋጁ ተቋማት ተልዕኳቸውን በብቃት፣ በጥራት እንዲፈፅሙ ያስችላል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ተቋማት ተልዕኳቸውን በብቃት፣ በጥራትና በውጤታማነት እንዲፈፅሙ የሚያስችል መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡ ምክር ቤቱ ባካሔደው 4ኛ…

ከተሞች የብልፅግና ተምሳሌት እንዲሆኑ ነዋሪዎች መትጋት አለባቸው- አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተሞችን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በሚከናወነው ሥራ ነዋሪዎች በባለቤትነት ስሜት ሊሰሩ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ አሳሰቡ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በተገኙበት በዎላይታ ሶዶ ከተማ የከተሞች የልማትና የመልካም…

በአማራ ክልል ተከስቶ የነበረውን የግሪሳ ወፍ መንጋ ከ90 በመቶ በላይ ማስወገድ ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሦስት ዞኖች ከተከሰተው የግሪሳ ወፍ መንጋ መካከል ከ90 በመቶ የሚልቀውን የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ማስወገድ መቻሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡ በቢሮው የሰብል ልማት ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር) እንዳሉት÷…

ጎንደር ከተማን ወደ ታሪካዊ ከፍታዋ የሚመልሱ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው – ም/ ጠ /ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጎንደር ከተማን ወደ ታሪካዊ ከፍታዋ የሚመልሱ የልማት ሥራዎች በፍጥነት እየተከናወኑ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውና የፌደራልና የክልል ከፍተኛ…

የፍልሰት ችግርን ለመቅረፍ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ነው-አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት የፍልሰትን ችግር ለመቅረፍ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን መከላከልን ጨምሮ የተቀናጀ ጥረት እያደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ፡፡ አራተኛው የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ሕብረት የጋራ የሥራ ቡድን…