Browsing Category
ቢዝነስ
ኤምባሲው በኢትዮጵያ ኢንቨስት የሚያደርጉ የጃፓን ባለሀብቶችን ቁጥር ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ተጨማሪ የጃፓን ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና ኢንቨስት እንዲያደርጉ በትኩረት እየሠራ መሆኑን በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ጋር…
አየር መንገዱ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አክሱም ከተማ አቋርጦት የነበረውን በረራ ዛሬ ዳግም ጀምሯል፡፡
ላለፉት ስድስት ወራት ሲካወኑ የነበሩ የጥገና ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ተከትሎ ነው አውሮፕላን ማረፊያ በዛሬው ዕለት ዳግም ለአገልግሎት ክፍት የሆነው፡፡…
ጉብኝቱ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እንድናይ ረድቶናል – የሳዑዲ ልዑክ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ያደረግነው ጉብኝት የኢንቨስትመንት ዘርፉን በጥልቀት ለመቃኘት ዕድል ሰጥቶናል ሲል የሳዑዲ ዓረቢያ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ከፍተኛ ልዑክ ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለልዑኩ አባላት በቢሾፍቱ የሚገኘውን አለማ ካውዳይስ…
ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕና ፋሬሲን ኩባንያ የ3 ሚሊየን ዩሮ የኮንትራት ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እና የጣልያኑ ፋሬሲን ኩባንያ የአልሙኒየም ፎርም ዎርክ ለማምረት የሚያስችል የ3 ሚሊየን ዩሮ የኮንትራት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት÷ የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን…
የኮሎምቢያው ኮንሴፕቶስ ኩባንያ በኢንቨስትመንት ተሰማርቶ የኮንስትራክሽን ግብዓት የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮንሴፕቶስ የተሰኘ የኮሎምቢያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በኢንቨስትመንት በመሰማራት ካገለገሉ የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶች ለኮንስትራክሽን የሚሆኑ ግብዓቶችን የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን…
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ2 ሺህ 700 ጊጋ ዋት ሠዓት በላይ ኃይል አመነጨ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባለፉት አሥር ወራት ከ2 ሺህ 700 ጊጋ ዋት ሠዓት በላይ ኃይል ማመንጨቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
በሁለት ተርባይኖች ኃይል እያመነጨ የሚገኘው ግድቡ÷ ባለፉት አሥር ወራት ከዕቅዱ የ26 በመቶ ብልጫ…
በጉምሩክ ኮሚሽን ሐዋሳ ቅርንጫፍ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አሥር ወራት 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ከተያዙት ዕቃዎች መካከልም÷ አልባሳት፣ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣…
የኢትዮ-ሳዑዲ ንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ሳዑዲ ንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በፎረሙ ላይም የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ የውጭ ጉዳይ…
ኢትዮጵያና ኮሪያ ሪፐብሊክ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ቃል ገቡ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኮሪያ ሪፐብሊክ ያላቸውን የፋይናንስ እና የኢኮኖሚ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ቃል ገብተዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከኮሪያ ሪፐብሊክ ኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ተቀዳሚ ምክትል ሚኒስትር ኪም ባይንግ-ህዋን ጋር ተወያይተዋል።…
ለውጭ ገበያ ከቀረበ የቡና ምርት 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 10 ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበ 210 ሺህ ቶን ቡና 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ የምታቀርበው የቡና…