Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ሀገራዊ ሪፖርት መሰረት አድርጎ በትሮይካ የሦስትዮሽ ቡድን የተዘጋጀው ሪፖርት ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ4ኛው ሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ግምገማ መድረክ ላይ ያቀረበችውን ሀገራዊ ሪፖርት መሰረት አድርጎ በትሮይካ የሦስትዮሽን የተዘጋጀው የተጠናቀረ ሪፖርት ጸድቋል፡፡ ኢትዮጵያ በ4ኛው ዙር የተባበሩት መንግስታት ሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች…

የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመገጣጠም ያለመ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመገጣጠም እና በቴክኒክ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመሥራት ያለመ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ ኤስ ጂ አውቶሞቲቭ ግሩፕ እና ሚስተር ሉታ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ናቸው፡፡…

ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን በጄክ ፖውል ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ58 ዓመቱ አሜሪካዊ የከባድ ሚዛን ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ከ27 ዓመቱ ጄክ ፖውል ጋር ባደረገው ግጥሚያ ተሸንፏል፡፡ ታይሰን ዛሬ ማለዳ ያደረገው ግጥሚያ ራሱን ከፕሮፌሽናል ውድድር ካገለለ ከ19 ዓመታት በኋላ የተከናወነ ነው፡፡ የግጥሚያውን…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢዝነስ ተጓዦች ዘርፍ ለ5ኛ ጊዜ ተሸለመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2024 የቢዝነስ ተጓዦች ሽልማት ውድድር ‘ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ’ በመባል ተሸለመ፡፡ ሽልማቱ በዘርፉ ለአምስተኛ ተከታታይ ዓመታት የተገኘ መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡ ከሽልማቱ በኋለም አየር…

ኢትዮጵያን ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ተመራጭ የጎብኚ መዳረሻ ለማድረግ በሚከናወነው ሥራ የቱሪስት እና የኮንፈረንስ ቪዛዎች ላይ እስከ 25 በመቶ ቅናሽ መደረጉ የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተመላከተ፡፡ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ለማበረታታት በ2016 ዓ.ም…

የጨው ንግድ ላይ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሞኖፖሊ አሠራር ተጋልጠው ከቆዩ ምርቶች መካከል ጨው አንዱ መሆኑን እና በዘርፉ ያለውን ችግር ለመቅረፍ እየተሠራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ በሀገራችን የንግድ ስርዓት ውስጥ ከሚስተዋሉ ችግሮች አንዱ…

ኢትዮጵያ ሶማሊላንድ ያካሄደችውን ዴሞክራሲዊ ምርጫ አደነቀች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ሶማሊላንድ ከትናንት በስቲያ ላካሄደችው ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ ምርጫ ለመንግሥቷ እና ሕዝቧ ያላትን አድናቆት ገለጸች፡፡ የሶማሊላንድ የምርጫ ኮሚሽን ሠላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ማካሄዱን በመጥቀስ ለዚህም ያላትን አድናቆት…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ነዋሪዎች ሰላምን ለማጽናት የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፎችን አካሄዱ። በሕዝባዊ ሰልፎ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን፤ ሰላምን…

የአፋር ፌዴራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች ለክልሉ ሰላም ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ፌዴራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ለአፋር ክልል መንግሥት አስረክበው ለክልሉ ሰላም እና ልማት በጋራ ለመሥራት ተስማሙ። የትጥቅ ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ በክልሉ አብአላ ከተማ መካሄዱን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ…

የአሜሪካ እና የቻይና ፕሬዚዳንቶች ፔሩ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የቻይና አቻቸው ሺ ዢንፒንግ በእስያ ፓስፊክ የኢኮኖሚክ ትብብር ጉባዔ ለመሳተፍ ፔሩ ሊማ ገቡ፡፡ ፕሬዚዳንቶቹ ሊማ ሲደርሱ በፔሩ አቻቸው ዲና ቦሉአርቴ  ደማቅ አቀባባል ተደርጎላቸዋል፡፡ በስልጣን ዘመን…