Fana: At a Speed of Life!

የሐረር ከተማን ዘመናዊ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ -አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረር ከተማን ዘመናዊ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት ሀረር ከተማን የሚያዘምኑ የቴክኖሎጂ ስርዓቶች እና መሰረተ ልማቶች…

የምርት ዘመኑ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት አበረታች መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምርት ዘመኑ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት አበረታች መሆኑን የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሰለሞን ላሌ ገለጹ፡፡ መንግስት ለግብርናው ዘርፍ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፈር ማዳበሪያን በኬንያ ላሙ በኩል…

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሳዓድ ሙባረክ ሳዓድ አል ጃፋሊ አል ናኢሚን ጋር ተወያዩ። በውይይታቸውም፤ የኢትዮ-ኳታር የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽንን አጠናክሮ ለማስቀጠል…

1 ሺህ 124 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 124 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል። በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት ውስጥ ዘጠኙ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ…

በመዲናዋ በሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት የተቀናጀ ተግባር እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ላይ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት የተቀናጀ ተግባር እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ። የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በመቀናጀት…

የሕብረተሰብ ተወካዮች አጀንዳቸውን ለይተው ለኮሚሽኑ አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት 21 ጀምሮ ላለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ሲያስተባብር የነበረውን ክንውን ጨርሷል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ወኪሎች በአጀንዳ ሀሳቦች…

በነ ዮሐንስ ቧያለውና ወንደሰን አሰፋ (ዶ/ር) መዝገብ የቀረበውን አቤቱታ ማረሚያ ቤቱ እንዲያስተካክል ታዘዘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በነ ዮሐንስ ቧያለው እና ወንደሰን አሰፋ (ዶ/ር) መዝገብ ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር የቀረበ አቤቱታን ተከትሎ ማረሚያ ቤቱ ማስተካከያ እንዲያደርግ ታዘዘ። ትዕዛዙን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ህገ-መንግስታዊና…

እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በሞት ፍርድ እንዲቀጣ የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉሳኔ አሳለፈ። በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍል ከተማ በተለምዶ ደካ አዲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ…

ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከጋቪ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊዘርላንድ ጀኔቫ እየተካሄደ ባለዉ 77ኛዉ የአለም ጤና ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ያሉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከግሎባል የክትባት ህብረት ኢኒሽዬቲቭ (ጋቪ) ጋቪ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሳኒያ ኒሽተር ጋር መክረዋል፡፡ በውይይታቸውም…

ብሔራዊ የህፃናት መረጃ አያያዝ ስርዓት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ የህፃናት መረጃ አያያዝ ስርዓት በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል፡፡ የመረጃ አያያዝ ስርዓቱ በተቋማት መካከል አገልግሎት ለሚፈልጉ ህፃናት ቀልጣፋ የቅብብሎሽ ስርዓት እንዲኖር፣ አገልግሎት የሚሹ ህፃናትን ምስጢር ለመጠበቅ፣ ግላዊነትና ከተጨማሪ…