Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ዘንድሮ 169 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይጠበቃል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ከዘንድሮው የመኸር ሰብል 169 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ። በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ የተመራ ልዑክ በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ እና ጃማ ወረዳዎች የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡…

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወባ ሥርጭት ሊጨምር ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስከ ታኅሣስ ወር 2017 ዓ.ም ድረስ የወባ በሽታ ሥርጭት ሊጨምር ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ጥሪ አቀረበ፡፡ የወባ በሽታን ሥርጭትን አስመልክቶ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና በክልሉ በየደረጃ ከሚገኙ…

የኢትዮ-እስራኤል ኢኖቬሽን ሳምንት በተለያዩ ዝግጅቶች መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው የኢትዮ-እስራኤል ኢኖቬሽን ሳምንት በተለያዩ ዝግጅቶች መካሄድ ጀምሯል፡፡ ዝግጅቱ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መስክ በኢትዮጵያና እስራኤል መካከል ያለውን ፈጠራ እና ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ያለመ ሲሆን ለአራት…

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ኢምፖርት ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ በቻይና ዓለምአቀፍ ኢምፖርት ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈች ነው። ከኤክስፖው ጎን ለጎንም የሀገራት መሪዎች በዓለም ንግድና ኢንቨስትመንት እየመከሩ ነው። ዛሬ በሻንጋይ በተከፈተውና 77 ሀገራትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በሚሳተፉበት ኤክስፖ…

የአዕምሯዊ ንብረት ሳምንት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃገራዊ የአዕምሯዊ ንብረት ሳምንት እየተከበረ ነው፡፡ ሁነቱ የዓለም አቀፍ የአእምሯዊ ንብረት ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስትና ከጃፓን የፈጠራ ባለቤት ማረጋገጫ ቢሮ እንዲሁም የኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።…

በአማራ ክልል የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ወደ 75 በመቶ ማደጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ባለፈው በጀት ዓመት የ73 በመቶ የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ወደ 75 በመቶ ማሳደጉን የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ጥላሁን ሽመልስ÷ በ2016 በጀት ዓመት 900 የሚሆኑ የውሀ ተቋማት…

የአሜሪካ ምርጫ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ምርጫ ለሀገሪቱ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ግምት ተሰጥቶት የብዙዎችን ትኩረት ይስባል። ሰዓታት የቀሩት የአሜሪካ ምርጫ ካማላ ሀሪስና የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ብርቱ ፉክክር እያደረጉበት…

በኮንትሮባንድ ሊገቡ የነበሩ ከ83 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ስልኮች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በተሽከርካሪ የተለያዩ ክፍሎች በመደበቅ በኮንትሮባንድ ሊገቡ የነበሩ 83 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመቱ ከ4 ሺህ 100 በላይ ስማርት የሞባይል ስልኮች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን ገለጸ፡፡ የኮንትሮባንድ እቃው የተያዘው በተሽከርካሪ ጋቢና ጣራ…

በሐዋሳ የኮሪደር ልማት ስራ ለመሳተፍ መዘጋጀቱን የሞሀ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አ.ማ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐዋሳ ከተማ በተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ ከመንግስት ጋር በመቀናጀት ለማልማት መዘጋጀቱን የሞሀ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል፡፡ የክሲዮን ማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል ሙሄ÷ድርጅቱ በኮሪደር ልማቱ…

የቱሪዝም ሚኒስትሯ የፋሲል አቢያተ መንግስት የጥገና ሂደትን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የፋሲል አቢያተ መንግስት የጥገና ሂደትን እየጎበኙ ነው። ሚኒስትሯ በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችንም ተመልክተዋል። በዚሁ ወቅት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ÷ በጎንደር አብያተ መንግስት…