Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለእስራኤል የአየር ሀይል ድጋፍ ማድረጓን ገለፀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ትናንት ምሽት እስራኤል በኢራን የተተኮሱ ሚሳኤሎችን እንድታከሽፍ የጸረ- ባላስቲክ ሚሳኤል ድጋፍ ማድረጓን አስታወቀች፡፡ በፔንታጎን መግለጫ የሰጡት የአሜሪካ መከላከያ ሃይል ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ፓትሪክ ራይደር÷ ወደ ቴል አቪቭ…

የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ደህንነትና ስራዎች ላይ ያተኮረ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2024 ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ደህንነት እና ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ጉባኤ በሞሮኮ ማራኬሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ጉባኤው፥ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂን ለአስተማማኝ እና ቀልጣፋ ስራዎች በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ…

በታይላንድ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ከ20 በላይ ህጻናት ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በታይላንድ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ከ20 በላይ ህጻናት ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተገልጿል፡፡ ከታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ ወጣ ብሎ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተጋጭቶ በእሳት መያያዙም ነው የተጠቆመው፡፡ አደጋው…

የእስራኤል እግረኛ ሰራዊት የአጭር ጊዜ ተልዕኮ በመያዝ ሊባኖስ ገባ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል ሄዝቦላህን ለማጥቃት የአጭር ጊዜ ተልዕኮ በመያዝ እግረኛ ሰራዊቷን ወደ ሊባኖስ ማስገባቷን አስታወቀች፡፡ እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ የተገደበና ዒላማ ያለው የምድር ላይ ተልዕኮ ብላ የገለጸችውን በእግረኛ ሰራዊቷ የሚከናወን ዕቅዷን ይፋ…

ኢትዮጵያ ለዘመናዊ አስተዳደር ሥርዓት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የ70 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ከዓለም ባንክ ጋር ተፈራረመች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለዘመናዊ አስተዳደር ሥርዓት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል የ70 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ስምምነት ከዓለም ባንክ ጋር ተፈራርማለች፡፡ ገንዘቡ በረጅም ጊዜ የሚከፈል ሲሆን በኢትዮጵያ የአስተዳደር ስራዎችን ለማቀላጠፍና ለማዘመን ሥራ…

ምሁራን የኢሬቻን እሴቶች ለማጎልበት እንዲሠሩ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘርፉ ምሁራን የኢሬቻን እሴቶች እና መልካም ገጽታዎች የሚያጎሉ ሥራዎችን እንዲሠሩ የኦሮሚያ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ጥሪ አቀረበ፡፡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳር ጽሕፈት ቤት ያዘጋጀው የ ‘ጉሚ በለል’ የውይይት መድረክ 'ኢሬቻ ለባህል…

የትግራይ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላሙን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ከፍጻሜ እንዲደርሱ ሕዝቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላሙን እንዲጠብቅ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መሥተዳድር ጌታቸው ረዳ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ርዕሰ መሥተዳድሩ በትግራይ ደቡብ ምሥራቅ ዞን በሕዝብ ከተወከሉ የተለያዩ…

በሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 4 በመውጣት አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በበርሊን 2024 የሴቶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 4 በመውጣት አሸንፈዋል፡፡ በዚሁ መሠረት አትሌት ትዕግስት ከተማ ርቀቱን 2 ሠዓት ከ16 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ በመግባት አሸንፋለች፡፡ እንዲሁም አትሌት መስታወት…

አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ የለማውን የማሽላ ኢንሼቲቭ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች በክልሉ በኩታ ገጠም የለማውን የማሽላ ኢንሼቲቭ ጎበኙ፡፡ "መልካም" የተባለውና ከፍተኛ ምርት የሚሰጠውን ማሽላ በክልሉ የማስፋፋት ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።…

ከንቲባ አዳነች አቤቤ 75 የመኖሪያ ቤቶችን ለነዋሪዎች አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ ክፍለ ከተማ ባለ 5 ወለል 75 የመኖሪያ ቤቶችን ለነዋሪዎች አስተላለፉ፡፡ በዊንጌትና ገብስ-ተራ የቀበሌ ቤቶችን በማፍረስ ለመኖር ምቹ የሆኑ 75 የመኖሪያ ቤቶች ያላቸው ባለ 5 ወለል…