Fana: At a Speed of Life!

የምክክር ኮሚሽኑ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብና ውይይት ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብና ውይይት ማካሄድ መጀመሩ ተገልጿል፡፡ ኮሚሽኑ የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፉን በቦንጋ ከተማ ጀምሯል፡፡ በዚህም በክልሉ ከሚገኙ 57 ወረዳዎች በኮሚሽኑ የተለዩ…

በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ ልዑክ ኳላላምፑር ከተማን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ማሌዢያ ኳላላምፑር ከተማን ጎብኝቷል፡፡፡ ልዑኩ በትናንትናው ዕለት ኳላላምፑር፣ ሳይበርጃን እና ሳንዌይ ከተሞችን የጎበኘ ሲሆን ፥ በዛሬው እለት ደግሞ…

አየር መንገዱ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤ350-1000 የመንገደኞች አውሮፕላን ከሁለት ቀናት በኋላ ይረከባል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤ350-1000 የተሰኘውን የመንገደኞች አውሮፕላን ከሁለት ቀናት በኋላ ይረከባል፡፡ አየር መንገዱ ከኤር ባስ ኩባንያ የሚረከበው ”Ethiopia Land of Origins” በሚል መጠሪያ…

ሰዎችን ማሰርና መደብደብን ጨምሮ በተደራራቢ ወንጀሎች የተከሰሱ እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰዎችን ያለአግባብ በማሰር፣ በመደብደብ እና ገንዘብ በመቀበል ተደራራቢ ወንጀሎች የተከሰሱ ሰባት ግለሰቦች እድሜ ልክ በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ወሰነ፡፡ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን…

ትምህርት ሚኒስቴር የሪሚዲያል ፕሮግራም ተቋርጧል በሚል ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን አስገነዘበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተማሪዎች አቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተቋርጧል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ትምርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች አቅማቸውን በማሻሻል ወደ…

አቶ እንዳሻው ጣሰው የተለያየ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የሕክምና ማዕከልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው በቡታጅራ ከተማ የተለያየ የሕክምና አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን ግራር ቤት ተሀድሶ ማዕከል ጎበኙ፡፡ በጉብኝታቸውም የማዕከሉን የሥራ እንቅስቃሴ፣ በማዕከሉ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶችን…

ከ700 በሚልቁ ሕገ-ወጥ የንግድ ተቋማት ላይ ርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ700 በሚልቁ ሕገ-ወጥ የንግድ ተቋማት ላይ ርምጃ መወሰዱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዳንኤል ዳምጠው አስታወቁ፡፡ በቢሮው የኢንስፔክሽን ቡድን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በንግድ እንቅስቃሴው ላይ ክትትል…

የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ ተሳታፊዎች የጤና ተቋማትን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ26ኛው ሀገር አቀፍ የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ ተሳታፊዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ወረዳዎችና ከተሞች የሚገኙ የጤና ተቋማትን እየጎበኙ ነው፡፡ በጉብኝታቸውም በተለያዩ የጤና ተቋማት ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የሕክምና ግብዓት እና…

በክልሉ ያሉ የመንገድ ልማት ስራዎች ለኢንቨስትመንት እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ አላቸው – ወ/ሮ አለሚቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)በክልሉ እየተሰሩ የሚገኙ የመንገድ ልማት ስራዎች ለኢንቨስትመንት እድገት አስተዋጽዖቸው የጎላ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሙድ ገለጹ፡፡ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በክልሉ እየተከናወኑ…

በሚቀጥሉት ቀናት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣዮቹ 10 ቀናት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ በሌላ በኩል በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና…